ሹመት / ክላራንስ ሲዶርፍ የአንድ የላሊጋ ክለብ አሰልጣኝ ተደርጎ ተሾመ

የቀድሞ የአያክስ፣ማድሪድ እና የሚላን ኮከብ የነበረው ሆላንዳዊው ክላራንስ ሲዶርፍ ወደ አሰልጣኝነት በመመለስ የአንድ የላሊጋ ቡድን አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ።

<!–more–>

የእግርኳስ ወዳጆች 2004 ላይ የነበረው ዲፖርቲቮ ላካሮኛ ፈፅሞ አይረሱትም።በተለይ በቻምፕየንስ ሊጉ በሚላን 4-1 ተሸንፈው በሜዳቸው 4-0 አሸንፈው ጨዋታውን የቀለበሱበት ወቅት የሚታወስ ነው።

የቀድሞ የላሊጋ ጠንካራው ቡድን አሁን ያ ጥንካሬው ታሪክ ሆኖ በላሊጋው ላለመውረድ እየተንገዳገደ ይገኛል።

ዘንድሮም እንዲሁ ላለመውረድ እየታገለ የሚገኝ ቡድን ሲሆን በሳምንቱ መጨረሻ በሪያል ሶሴዳድ 5-0 ከተሸነፉም በኋላ አሰልጣኙን ክሪስቶባል ፓራሎን አሰናብቷል።

አሰልጣኙን ተክቶ ወደ ዲፖርቲቮ ያቀናው ደግሞ የቀድሞ ተጫዋች ሆላንዳዊው ክላራንስ ሲዶርፍ እንደሆነ የታወቀ ሲሆን ክለቡንም እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ድረስ እንዲመራ ሀላፊነቱን ተረክቧል።

የ 41 አመቱ ሲዶርፍ 18ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን እንዲሁም ባለፉት ሰባት ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻለውን ዲፖርቲቮን ከወራጅ ስጋት ማላቀቅ የመጀመሪያ ስራው ይሆናል።

አራት ጊዜ የቻምፒየንስ ሊግ ማሸነፍ የቻለው ሲዶርፍ ሚላንን እንዲሁም የቻይናውን ሼንዜን ማሰልጠን ችሎ እንደነበር ይታወሳል።

Advertisements