የተረጋገጠ / ሊቨርፑል ትልቅ አድናቆት የተሰጠውን ተስፈኛ ታዳጊ አስፈረመ

ሊቨርፑል ትልቅ አድናቆት የተሰጠውን የ 18 አመቱን ተስፈኛ ተከላካይ አንደርሰን አሮዮን ከኮሎምቢያው ክለብ ፎርታሌዛ አስፈርሟል።

አሮዮን የቀዮቹ ተጫዋች መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላም ለቀጣዮቹ 18 ወራት በስፔን ሶስተኛ ዲሺዚዮን ለሚጫወተው ማዮርካ በውሰት እንደሚሰጥ የተገለፀ ሲሆን ሊቨርፑል ታዳጊውን ወደቡድኑ ለማምጣትና ለማጫወት የስራ ፈቃድ ወረቆቶችን መጨረስ እንዳለበትም ታውቋል። 

ሊቨርፑል እንዳለው ከሆነ በተጫዋቹ ዝውውር ዙሪያ በዚህ እየተጠናቀቀ ባለው የጥር ወር ከስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን ተስፈኛው ታዳጊም ወደጀርመን አቅንቶ ከነበረው የክለቡ ከ 18 አመት በታች ስብስቡ ጋር የሙከራ ጊዜ እንዳሳለፈ ተነግሯል። 

አሮዮን እድሜው ገና 20 ባይደፍንም ከ 15 አመቱ አንስቶ ለተጫወተበት ፎርታሌዛ 22 ጨዋታዎችን ማድረግ ሲችል የሀገሩ ኮሎምቢያ ከ 17 እና 20 አመት በታች ቡድኖችን  መክሎ መጫወትም ችሏል።

Advertisements