ኤደን ሀዛርድ የቼልሲ አቋም መውረድ ምክንያት አሳወቀ

ኤደን ሀዛርድ የ2016/2017 የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ አሸናፊ የነበረው ቼልሲ በአስገራሚ መልኩ አቋሙ የወረደበትን ምክንያት ተናግሯል።

የአንቶኒዬ ኮንቴው ቡድን አምና ሻምፒዬን ሲሆን የነበረውን ብቃት ዘንድሮ ለማግኘት ተቸግሯል።ከዋንጫ ፉክክሩም በጊዜ በመውጣቱ እቅዱ በቻምፒየንስ ሊጉ ላይ የሚያሳትፈውን ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ ሆኗል።

በዚህ የቡድኑ ውጤትም አሰልጣኙ ከፍተኛ ጫና ውስጥ በመውደቃቸው በቀጣይ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች የቆይታቸው እጣ ፈንታ የሚወሰን ይሆናል።

አማካዩ ኤደን ሀዛርድም የቡድኑ አቋም መውረድ በክረምቱ የገቡ እና የወጡ ተጫዋቾች ምክንያት በክለቡ የተፈጠረ ብዙ ለውጦች መሆኑን አሳውቋል።

“በክረምቱ ብዙ ነገሮችን ተለውጠዋል።ተጫዋቾች ለቀዋል፣በምትካቸውም ሌሎች ተጫዋቾች ቡድኑን ተቀላቅለዋል።” በማለት በክለቡ የተፈጠሩ ለውጦች ለቡድኑ መዳከም እንደ ምክንያትነት አቅርቧል።

ሀዛርድ አንድ ቡድን ብቻ ሁሌ ቢያሸንፍ ውድድሩ አሰልቺ እንደሚሆንም ጨምሮ ተናግሯል።

“እግርኳስን የምንወደው ለዚህ ነው።ሁልጊዜ አንድ ቡድን ብቻ የሚያሸንፍ ከሆነ አሰልቺ ይሆናል።ለዚህም ነው እግርኳስ የተለየ የሆነው።በእንግሊዝ ምን ሊፈጠር እንደሚችል የሚታወቅ ነገር የለም።” በማለት ሀሳቡን ሰጥቷል።

Advertisements