አቀባበል / ሪያድ ማህሬዝ በዛሬው ዕለት ወደልምምድ እንደሚመለስ ተገለፀ


ሪያድ ማህሬዝ በዛሬው ዕለት ወደ ልምምድ እንደሚመለስ እና በነገው ዕለትም ሌስተር ከ ማንችስተር ሲቲ በሚያደርገው ጨዋታ በቡድኑ ሊካተት እንደሚችል ተገልጿል። 

አልጄሪያዊው ኮከብ ወደሲቲ ሊያደርገው የነበረው ዝውውር ውድቅ ከሆነበት በኋላ ከቀበሮዎቹ ጋር ልምምድ ሳይሰራ እና ጨዋታ ሳያደርግ ቀናትን አስቆጥሯል። 

የክለቡ አሰልጣኝ ክላውድ ፒኤል በትናንቱ ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ነገሮች ገና እንዳልተረጋጉ በመግለፅ ማህሬዝ በኢትሀድ የሚደረገው ጨዋታ ሊያመልጠው እንደሚችል እንደሚችል ተናግረዋል።

ፑኤል ተጫዋቹ ወደቡድናቸው እንዲመለስ መንገዱን መክፈት የፈለጉ ቢመስሉም ግን ማህሬዝ በቅዳሜው ጨዋታ ላይ የተሰላፊነት ቦታን የማግኘቱ ነገር በቀጣይ የሚታይ ነው።

ማህሬዝ ለመጨረሻ ጊዜ ለቀበሮዎቹ ተሰልፎ መጫወት የቻለው ጥር 12 ሌስተር ዋትፎርድን 2-0 በረታበት እና የቡድኑን ሁለተኛ ግብ ባስቆጠረበት ዕለት ነው። 

Advertisements