ጆሴ ሞሪንሆ ማንችስተር ዩናይትድ ዴቪድ ዴሂያን የመሸጥ ፍላጎት እንደሌለው ተናገሩ

በክረምቱ ወደ ማድሪድ የማቅናት እድል እንዳለው እየተነገረ የሚገኘው ዴቪድ ዲሂያን በተመለከተ ጆሴ ሞሪንሆ “ዩናይትድ ትላልቅ ተጫዋቾችን የሚስብ እንጂ የሚሸጥ አይደለም”ሲሉ አጣጥለውታል።

የማንችስተር ዩናይትድ ቁልፍ ተጫዋች የሆነው ዴቪድ ዲሂያ አሁንም የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች መሆኑን ቀጥሎበታል።

የሀገሩ ክለብ የሆነው ማድሪድም በክረምቱ ለውጥ ሊያደርግባቸው ካሰባቸው ቦታዎች ውስጥ የግብ ጠባቂ ቦታ በመሆኑ ትኩረታቸውን ካለፉት አመታት ጀምሮ ካደረጉባቸው ተጫዋቾች ውስጥ አንዱ ዴሂያ ነው።

ማድሪድ በግብ ጠባቂነት ቦታ ላይ ሌላ ትኩረት ያደረጉበት ቲቦ ኮርቱዋ ሲሆን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ላይ ከሁለቱ አንዱን ለማስፈረም እንደሚንቀሳቀሱ ይጠበቃል።

በጉዳዩ ላይ ሀሳባቸውን የሰጡት ጆሴ ግን ተጫዋቹን የመልቀቅ ፍላጎት እንደሌላቸው ተናግረዋል።

“ስለ ኩርቱዋ መናገር አልፈልግም።ትላልቅ ተጫዋቾችን ለመሳብ የሚሞክር ቡድን ምርጥ ተጫዋቹን ለመሸጥ ይዘጋጃል ብላችሁ ታስባላችሁ?”

“በዛ ደረጃ መገኘታችን ለማወቅ ከፈለጋችሁ አሌክሲስ ሳንቼዝ፣ማቲች፣ፖግባን የመሳሰሉትን ማዘዋወር እንደቻልን መመልከት ትችላላችሁ ስለዚህ ትላልቅ ተጫዋቾቻችን ለመልቀቅ አንፈቅድም።” በማለት ዴሂያ  የመሸጥ ፍላጎት እንደሌላቸው ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

Advertisements