ላካዜቲ በኦውባምያንግ ምክንያት በራስ መተማመኑ ሳይቀንስ እንዳልቀረ ቬንገር ተናገሩ

የአርሰናሉ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር ፈረንሳያዊው አጥቂ አሌክሳንደር ላካዜቲ የፒየር-ኤመሪክ አውባምያንግን በጥር ወር ወደክለቡ መምጣትን ተከትሎ በራስ መተማመኑ ሳይጠፋ እንዳልቀረ እምንታቸውን ገልፀዋል።

ላካዜቲ አርሰናል ቅዳሜ ቀትር ላይ በፕሪሚየር ሊጉ በቶተንሃም 1ለ0 በተሸነፈበት ጨዋታ ከተቀያሪ ወንበር ላይ ተነስቶ ወደሜዳ በመግባት በጨዋታው መገባደጃ ሰዓት በጣም ጥሩ የሚባል የማግባት ዕድል አምክኗል።

ፈረንሳያዊው ተጫዋች በ53 ሚሊዮን ዩሮ በኃምሌ ወር ከሊዮን አርሰናልን ከተቀላቀለበት ጊዜ አንስቶ በሁሉም ውድድሮች ላይ ባደረጋቸው 29 ጨዋታዎች ማስቆጠር የቻለው ዘጠኝ ግቦችን ብቻ ነው።

አርሰናል 56 ሚሊዮን ፓውንድ እንደሆነ በተነገረ ዋጋ በጥር ወር ኦውባምንያንግን ካስፈረመ ጊዜ አንስቶም ቬንገር የላካዜቲ በራስ መተማመን ሳይመናማን እንዳልቀረ ተናግረዋል።

“እሱ ከግብ ጠባቂ ጋር አንድ ለአንድ ሲጋናኝ ጥሩ ግብ አስቆጣሪ ነው።” ሲሉ ቬንገር ተናግረው። “ከዚያ ባፊት በአስቸጋሪ ጊዜያቶች ውስጥ አልፏል። ልምምዱንም ሆነ አጨራረስ ለይ ጠንክሮ ነው የሚሰራው። 

“ምን እንደሆነ አላውቅም። ኳሷን በሚገባ ሳይነካት ቀርቶ ይሆን? እንደዚያ ሊሆን ይችላል። [ሙከራው] በሰከንዶች ሽርፍፊ ጊዜ ውስጥ የተከሰተ ነበር። 

“ምናልባት በራስ መተማመኑ ከፍ ሳይል ቀርቶ ሊሆን ይችላል። ምክኒያቱም ተቀናቃኝ የመጣበት መሆኑ ስለተመለከተ ሊሆን ይችላል።” 
በማለት ቬንገር ገልፀዋል።

አርሰናል በዩሮፓ ሊግ የመጨረሻዎቹ 32 ክለቦች በሚፋለሙባት ዙር ኦስቴርሰንስን ሃሙስ ምሽት ይገጥማል።

Advertisements