አርሰን ዌንገር በዩሮፓ ሊግ የጥሎማለፍ ጨዋታ ላይ ተጫዋቾቻቸውን እንደማያሳርፉ ተናገሩ

በቀጣይ አመት በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ላይ ለመሳተፍ ሌላኛው አማራጫቸውን በሚገባ ለመጠቀም ያሰቡት አርሰን ዌንገር በቀጣይ ሳምንት የሚያደርጉት የዩሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታቸው ላይ ተጫዋቾቻቸውን እንደማያሳርፉ ተናግረዋል።

<!–more–>

መድፈኞቹ ዘንድሮ በፕሪምየርሊጉ እስከ አራተኛ ደረጃን ይዞ ለማጠናቀቅ እስካሁን ድረስ በጥሩ ቦታ ላይ ተረጋግተው አልተገኙም።

ባለፈው ቅዳሜም በጎረቤታቸው ቶተንሀም ሆትስፐሮች ከተሸነፉ በኋላ እስከ አራት አጠናቀው የአውሮፓን ቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎን የማግኘት እድላቸው እየጠበበ መጥቷል።

በቀጣይ ቀሪ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ጠንክረው መቅረብ የሚገባቸው አርሰናሎች እድላቸውን በራሳቸው ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ከፊታቸው የሚገኙት ቡድኖች ውጤት ጭምር መመልከት ይጠበቅባቸዋል።

ይህን በሚገባ የተረዱት አርሰን ዌንገር በዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ላይ ጠንካራ ቡድናቸውን ይዘው ለመቅረብ እንደተዘጋጁ አሳውቀዋል።

በተለይ ደግሞ በቀጣይ ሳምንት የሚካሄደው የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ ላይ ቀደም ብለው ከውድድሩ በጊዜ መሰናበታቸውን ተከትሎ የሚያደርጉት ጨዋታ ባለመኖሩ ሙሉ ትኩረታቸውን ወደ ስዊድን አቅንተው የሚያደርጉት የዩሮፓ ሊግ ጨዋታን አድርገዋል።

በነዚህ ምክንያቶች ዌንገር በዚህ ጨዋታ ላይ ጠንካራ ቡድናቸውን እንደሚያሰልፉ አሳውቀዋል።

“ለዩሮፓ ሊግ ጨዋታው ሁሉን ነገር እናደርጋለን።ምክንያቱም በሁለቱ ጨዋታዎች መካከል ሌላ ጨዋታ አናደርግም።በጨዋታው ዋናው ቡድኔን አሰልፋለው፣ ምክንያቱም በኤፍ ኤ ካፕ ስለማንጫወት አንዱ መልካም ጎን ነው።ተጨዋቾቼን ላሳርፍ የምችልበት ምንም አይነት ምክንያት የለኝም።” ሲሉ ተናግረዋል።

 

Advertisements