ከበርቴዎቹ / በአለማችን ውድ ስብስብ ያላቸው 100 ክለቦች ይፋ ሆኑ

ማንችስተር ሲቲ በ 778 ሚሊዮን ፓውንድ የአለም ውድ ስብስብን የያዘ ተብሎ በአንደኛነት መቀመጥ ችሏል።

ከአስር ምርጥ የአለም ውድ ክለቦች የመጀመሪያ ስድስቱን ደረጃ የፕሪምየር ሊጉ ክለቦች በተቆጣጠሩበት በዘንድሮው የአለም ውድ ክለቦች ዝርዝር ባሳለፍነው የጥር የዝውውር መስኮት አይሜሪክ ላፖርቴን ማስፈረም የቻለው ሲቲ የአለም ቀዳሚው ውድ ክለብ ሆኗል።

ሉካስ ሞራን በጥር የዝውውር መስኮት በ 25 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ቶትነሀም ያሻገረው የፓሪሱ ፒኤስጂ በበኩሉ በሁለተኛነት ተቀምጧል።

ፒኤስጂ የኤዲሰን ካቫኒ፣ የኔይማር 200 ሚሊዮን ፓውንድ እና ቀሪው ስብስቡ 713.2 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ በመያዝ ሶስተኛ ከተቀመጠው የኦልትራፎርዱ ማንችስተር ዩናይትድ በልጦ ተገኝቷል።

የካታላኑ ባርሴሎና በ 661.7 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ በሶስተኛነት ከተቀመጠው የጆሴ ሞውሪንሆ ስብስብ እና በ 524.4 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ በአምስተኛነት ከተቀመጠው ቼልሲ መሀከል ሆኖ የአራተኛ ደረጃን ይዞ ተገኝቷል።

ከአለም ምርጥ 100 ውድ ስብስብ ያላቸው ቡድኖች መሀከል ቶትነሀም በ12ኛነት፣ ሳውዝአምፕተን በ18ኛነት እና ክርስቲያል ፓላስ በ19ኛነት ተቀምጠዋል።

በዘንድሮው የውድነት ደረጃ መሰረትም የእንግሊዛውያን አማካኝ የአንድ ቡድን ዋጋ ከስፔን አቻዎቻቸው ከእጥፍ በላይ ብልጫ ያለው ነው። 

በዚህም መሰረት የአንድ የእንግሊዝ ክለብ አማካኝ የስብስብ ዋጋ 258 ሚሊዮን ፓውንድ ሲሆን የላሊጋው አማካኙ 110 ሚሊዮን ፓውንድ፣ የቡንደስሊጋ 100.1 ሚሊዮን ፓውንድ እና የፈረንሳይ ሊግ 1 በበኩሉ 86 ሚሊዮን ፓውንድ ነው።

ውድ ስብስብ ያላቸው የአለም አስር ቡድኖች  

 1. ማንችስተር ሲቲ – 778 ሚሊዮን ፓውንድ 

 2. ፒኤስጂ – 713.2 ሚሊዮን ፓውንድ

 3. ማንችስተር ዩናይትድ – 661.7 ሚሊዮን ፓውንድ 

 4. ባርሴሎና – 642.2 ሚሊዮን ፓውንድ 

 5. ቼልሲ – 524.4 ሚሊዮን ፓውንድ

 6. ሪያል ማድሪድ – 440.3 ሚሊዮን ፓውንድ

 7. ሊቨርፑል – 408.4 ሚሊዮን ፓውንድ

 8. ጁቬንቱስ – 396.9 ሚሊዮን ፓውንድ 

 9. አርሰናል – 357 ሚሊዮን ፓውንድ 

10. ኤቨርተን – 323.3 ሚሊዮን ፓውንድ

Advertisements