ክሎፕ 50ኛ የፕሪሚየር ሊግ ድል አስመዝግበዋል፤ ለመሆኑ ይህ ድል ምን ያህል ደረጃ ላይ ያስቀምጣቸዋል?

ሊቨርፑል ሳውዛምፕተንን ከሜዳው ውጪ 2ለ0 የረታበት ጨዋታ ክሎፕ በፕሪሚየር ሊጉ 50ኛ ድላቸው ሆኖ በመመዝገብ በሊጉ ይህን ያህል ድል በፈጥነት በማስመዝገብ በዘጠነኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ አሰልጣኝ አድርጓቸዋል።

የቀድሞው የዶርትሙንድ አሰልጣኝ ባደረጓቸው 95 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች 50ኛ ድላቸውን ያስመዘገቡ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ ብሬንዳን ሮጀርስ በአንፊልድ ቆይታቸው ሊቨርፑል ካስመዘገቡት የድል ቁጥር ጋርም ተመሳሳይ ነው። 

ይሁን እንጂ ሮጀርስ በስዋንሲ ሲቲ በነበራቸው ቆይታ ምክኒያት ግን ከአንድ እስከአስር ባለው ደረጃ ውስጥ መግባት ከቻሉ አሰልጣኞች ተርታ እንዳይካተቱ ምክኒያት ሆኗል።

የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሆዜ ሞሪንሆ በቼልሲ አሰልጣኝነት ዘመናቸው ከ63 ጨዋታዎች በአሰድናቂ ሁኔታ 50 ድሎችን ማስመዝገብ ችለው በፍጥነት 50ኛ የፕሪሚየር ድል በማስመዝገብ የቀዳሚነት ስፍራውን የነጠቃቸው አሰልጣኝ እስካሁን የለም። የቀድሞው የማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሪኒ በ2013-14 የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን በሆኑበት የውድድር ዘመን በ75 ጨታዎች 50ኛ ድለቸውን በመቀዳጀት ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።

በፕሪሚየር ሊጉ በቶሎ 50ኛ ድላቸውን ማስመዝገብ በመቻል ሌሎች ደረጃዎች የያዙት አሰልጣኞችን ደግሞ ከተከታዩ የኦፕታ የቁጥራዊ መረጃ ይመልከቱ።

1. ሆዜ ሞሪንሆ (63 ጨዋታዎች)
2. ማኑኤል ፔሌግሪኒ (75 ጨዋታዎች)
3. አሌክስ ፈርጉሰን (82 ጨዋታዎች)
4. ሮቤርቶ ማንቺኒ (83 ጨዋታዎች)
5. ኬኒ ዳልግሊሽ (91 ጨዋታዎች)
6. ኬቨን ኪጋን (92 ጨዋታዎች)
7. ረፋኤል ቤኒቴዝ (93 ጨዋታዎች)
8. አርሰን ቬንገር (94 ጨዋታዎች)
9. የርገን ክሎፕ (95 ጨዋታዎች)
10. ዴቪድ ኦ’ሊሪ (99 ጨዋታዎች)

Advertisements