የቀድሞ የናይጄሪያ ኮከብ ዳንኤል አሞካቺ የአለም ዋንጫ የሚያሸንፈው ሀገር አስገራሚ ግምቱን ሰጠ

ናይጄሪያ ካፈራቻቸው ምርጥ ተጫዋቾች ውስጥ አንዱ የነበረው ዳንኤል አሞካቺ የ2018 የአለም ዋንጫ አሸናፊ ሊሆን የሚችለው ሀገር በመጥቀስ አስገራሚ ግምቱን ሰጥቷል።

የ2018 የራሺያ የአለም ዋንጫ የፊታችን ሰኔ ወር ላይ ሊጀመር ጥቂት ወራት ብቻ ቀርተውታል።

ተሳታፊ ሀገራትም በሙሉ ተለይተው ከታወቁ በኋላ በስምንት ምድቦች 32 ሀገራት ተጋጣሚያቸው አውቀው የውድድሩን መጀመር በናፍቆት እየተጠባበቀ ይገኛሉ።

አፍሪካን ከሚወክሉ ውስጥ ደግሞ ናይጄሪያ አንዷ ስትሆን በውድድሩ ላይ ወጣቶችን ያካተተው ቡድኗ ምን ሊያሳይ እንደሚችል በጉጉት ይጠበቃል።

የቀድሞ የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው ዳንኤል አሞካቺም ከብሄራዊ ቡድኑ ትልቁን ውጤት እንደሚጠብቅ አሳውቋል።

አሞካቺ ናይጄሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የአለም ዋንጫን ታነሳለች በማለት አስገራሚ አስተያየት ሰጥቷል።

“እኔ ቁጥር አንድ የናይጄሪያ ደጋፊ ነኝ።በቡድናችን ውስጥም ብዙ አዳዲስ ትውልዶች አሉ።እነሱም ከልጅነታቸው ጀምረው በአካዳሚ አድገው ለብሔራዊ ቡድን መጫወት የቻሉ ናቸው። ከልጅነታቸው ጀምረው ኳስን ጠንቅቀው የተረዱ በመሆናቸው ተፅእኖ ፈጣሪነታቸው በማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ አሳይተዋል።” በማለት ናይጄሪያ የአለም ዋንጫን ታሸንፋለች በማለት አስገራሚ አስተያየቱን ሰጥቷል።

Advertisements