የቼልሲ ታሪካዊ ተጫዋቾች የክለቡን የ90ዎቹ የሶስትዮሽ ዋንጫ ድል መታሰቢያ የሚሆን ውድድር ሊያደርጉ ነው

የቼልሲ ታሪካዊ ተጫዋቾች የ1990ዎቹን የክለቡን ስኬት ለማስተወስ በማሰብ እንደማንችስተር ዩናይትድ፣ ሪያል ማድሪድ፣ ባርሴሎና እና ኢንተር ሚላን ከነበሩ ታሪካዊ ተጫዋቾች ጋር በውድድር ዘመኑ መጠናቀቅ በኋላ በስታንፎርድ ብሪጅ የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን ክለቡ በይፋዊ ድረገፁ ገልፅዋል።

ሰማያዊዎቹ ሊያደረጓቸው ካሰቧቸው ጨዋታዎች መካከል የመጀመሪያውን ጨዋታቸውን በ1998 የሶስትዮሽ ዋንጫ ባለቤት እንዲሆን ያስቻላቸውን ቡድን ይዘው ከኢንተር ሚላን የምንጊዜውም ተጫዋቾች ጋር እ.ኤ.አ. ግንቦት 18 የሚጫወቱም ይሆናል።

በዚህ ጨዋታ የቼልሲ የዘመኑ ታሪካዊ ተጫዋቾች ጂያንፍራንኮ ዞላ፣ ዴኒስ ዋይዝ፣ ቶሬ-አንድሬ ፍሎ፣ ግራም ለ ሳውክስ እና የክለቡ የተጫዋች አሰልጣኝ የነበረው ጂያንሉካ ቪያሊ የተካተተበትን ቡድን በመያዝ ከኢንተር ታሪካዊ ተጫዋቾች እንደኻቪየር ዛኔቲ፣ ዩሪ ጆርካይፍ እና ፍራንሲስኮ ቶልዶ የተካተቱበትን ቡድን የሚገጥሙ ይሆናል።

ይህ ጨዋታ የሊግ ካፕ፣ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ እና የሱፐር ካፕ አሸናፊ የነበረውን የዘመኑን ቼልሲን 20ኛ ዓመት የድል ዘመን ለማስታወስ የሚደረግ ነው።

አብራሃሞቪች ቼልሲን በባለቤትንነት በተረከበበት 2003 ክለቡ የሊጉን ዋንጫ ብቻ ማንሳት ችሎ የነበረ ቢሆንም ሩሲያዊው ባለሃብት ከዚያ ጊዜ በኋላ ተጨማሪ ከእንድ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ እና ሌሎች ዋንጫዎች በተጨማሪ አምስት የሊግ ዋንጫዎችን በማንሳትና ታላቅ ሽግግር በማድረግ ቼልሲን የዓለማችን የእግርኳስ ልዕለ ኃያል ክለብ ማድረግ ችሏል። 

ይሁን እንጂ ቼልሲ ባለፈው የውድድር ዘመን የሊጉ ሻምፒዮን ከሆነ በኋላ በዚህ የውድድር ዘመን ያለፉት ሁለት ጨዋታዎቹን በሰፊ ግብ በመሸነፍ መጥፎ የሚባል ጉዞ በማድረግ ላይ ይገኛል። ከአንድ እስከአራት ካለው ደረጃ ውጪ የሚገኝ ከመሆኑም ባሻገር በዚህ ደረጃ ውስጥ ገብቶ የውድድር ዘመኑን ለማጠናቀቅ እንደሊቨርፑል፣ ቶተንሃም እና አርሰናል ካሉ ክለቦች ከፍተኛ ፉክክር የሚጠብቀውም ይሆናል።

Advertisements