“ሊዮኔል ሜሲ ለባርሴሎና የሚያደርገውን የጨዋታ ቁጥር መቀነስ አለበት ” ክላውዲዮ ታፒያ

Image result for Lionel Messi

የአርጀንቲና እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ክላውዲዮ ታፒያ የብሄራዊ ቡድኑ አምበል ሊዮኔል ሜሲ ካሁን በኋላ ለባርሴሎና የሚያደርገውን የጨዋታ ብዛት እንቀንስ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡

በ2018 ሩሲያ ለምታስተናግደው የአለም ዋንጫ ውድድር ላይ በመጨረሻው ቀን  ሀገሩ አርጀንቲና እንድታልፍ ቁልፉን ሚና የተወጣው ሊዮኔል ሜሲ በአለም ዋንጫው በትኩስ ጉልበት እንዲመጣ ለባርሴሎና በቀጣይ የሚያደርጋቸውን የጨዋታ ብዛቶች መቀነስ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ሊዮኔል ሜሲ በውድድር አመቱ ባርሴሎና በሁሉም ውድድሮች ካደረጋቸው ሰላሳ ዘጠኝ  ጨዋታዎች መካከል ሰላሳ ሶስቱን ቋሚ ሆኖ የጀመረ ሲሆን በስፔን ላሊጋም ለመጨረሻ ጊዜ ከሁለት ሳምንታት በፊት ባርሴሎና ከኤስፓኞል ጋር 1-1 በሆነ አቻ ውጤት በተለያየበት ጨዋታም ከተቀያሪ ወንበር በመነሳት ጨዋታውን አድርጓል፡፡

ይህ ያሳሳባቸው የአርጀንቲና እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ክላውዲዮ ታፒያም  ከብሄራዊ ቡድኑ ዳይሬክተሮች እና የአሰልጣኝ ስታፍ አባላት ጋር በመሆን ሊዮኔል ሜሲ በቀጣይ ለባርሴሎና የሚያደርጋቸው የጨዋታ ብዛቶች ላይ ተጫዋቹን በማካተት እንደሚነጋገሩ ለቲዋይሲ ስፖርት ተናግረዋል፡፡

Advertisements