ስንብት / ሪያን ማሰን በጭንቅላት ጉዳት ምክንያት እራሱን ከእግር ኳስ አገለለ

የሁል ሲቲው ሪያን ማሰን ባሳለፍነው አመት ጥር በጭንቅላቱ ላይ በደረሰበት ጉዳት የተነሳ ገና በለጋ እድሜው ከእግር ኳስ ለመገለል ተገዷል።

ማሰን ቡድኑ በስታምፎርድ ብሪጅ በነበረው ጨዋታ ከሰማያዊዎቹ ተከላካይ ጋሪ ካሂል ጋር በመጋጨቱ የጭንቅላት ቅል መሰንጠቅ ደርሶበት ላለፈው አንድ አመት ከሜዳ ተገሎ ቆይቷል። 

የቀድሞው የእንግሊዛዊ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ከአደጋው ጋር በተያያዘ በህክምና ሰዎች የተሰጠውን ምክር መሰረት አድርጎም እራሱን ከእግር ኳስ ማሰናበቱ ተነግሯል።

ማሰን በ 2014 በቶትነሀም ሳለ የመጀመሪያ ቡድን ተሰላፊነትን እድል ማግኘት ከጀመረ ወዲህ 69 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን ለቀድሞው ክለቡ ማድረግ የቻለ ነው።  

የ 26 አመቱ ተጫዋች ከእግር ኳስ መሰናበቱን ባረጋገጠበት መግለጫው “እራሴን ከፕሮፌሽናል እግር ኳስ እንዳገል ከህክምና ሰዎች ባገኘሁት ምክር መሰረት እራሴን ከእግር ኳስ አግልያለሁ።” ብሏል።


Advertisements