“ኔይማርን በማድሪድ ማሊያ ማየት አልፈልግም ” – የስፔን ጠቅላይ ሚኒስቴር

ብራዚላዊው ኔይማር ከአንድ አመት የፓሪስ ቆይታው በኋላ ወደ ስፔን ተመልሶ ሪያል ማድሪድን እንደሚቀላቀል እየተነገረ ባለበት ወቅት የስፔን ጠቅላይ ሚኒስቴር የሆኑት ማሪያኖ ራሆይ ተጫዋቹን በማድሪድ ማሊያ ሊመለከቱት እንደማይፈልጉ አሳውቀዋል።

ወደ ፔዤ ካቀና ቦሀላ ከደጋፊዎች እና ከቡድን አጋሮቹ ጋር ጥሩ የሆነ ስሜት ውስጥ የማይገኘው ኔይማር በክረምቱ ወደ ማድሪድ የማቅናት እድል እንዳለው እየተነገረ ይገኛል።

ተጫዋቹን ለማዘዋወር ፔዤ የአለም የዝውውር ሪከርድ በሆነ የዝውውር ሂሳብ በመክፈል ወደ ፓሪስ ቢያመጣውም የተጫዋቹ ቆይታ በክለቡ የቻምፕየንስ ሊግ ውጤት ላይ ተመርኩዞ እንደሆነ ተሰምቷል።

ከሳምንት በፊት በወጣው መረጃ መሰረት ፔዤ የቻምፒየንስ ሊግን ዋንጫ ማንሳት የሚችል ከሆነ ኔይማር ሪያልማድሪድ እንዲገባ እንደሚለቀው ታውቋል።

የወቅቱ የማድሪድ አንዳንድ ተጫዋቾች ኔይማር ወደ ክለባቸው ቢመጣ መልካም እንደሚሆን ቢናገሩም የስፔን ጠቅላይ ሚኒስቴር የሆኑት የማድሪድ ደጋፊው ማሪያኖ ራሆይ ግን ተጫዋቹን በክለባቸው ማሊያ ሊያዩት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል።

“ኔይማርን በነጩ ማሊያ ልመለከተው አልፈልግም።” ሲሉ ተጫዋቹ በክለባቸው ሲጫወት ለማየት እንደማይፈልጉ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

ማድሪድ እና ፔዤ በአውሮፓ ቻምፕየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ጨዋታ ነገ የሚያደርጉ ይሆናል።

Advertisements