አስደንጋጭ / አሌክሳንደር ላካዜቲ ለስድስት ሳምንታት ያህል ከሜዳ ይርቃል

የአርሰናሉ አጥቂ አሌክሳንደር ላካዜቲ ቀላል የጉልበት ቀዶ ጥገና ማድረጉን ተከትሎ ለስድስት ሳምንታት ያህል ጊዜ ከሜዳ ይርቃል።

ባሳለፍነው ክረምት የጊዜው የአርሰናል የክብረ ወሰን የዝውውር ዋጋ በሆነ 52 ሚሊዮን ፓውንድ አርሰናልን የተቀላቀለው ፈረንሳዊ ኮከብ በግራ እግሩ ላይ ከገጠመው የጉልበት ጉዳት ጋር በተያያዘ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ተገዷል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም ሀሙስ ምሽት በኢሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ላይ በፊት መስመር ላይ አርሰን ቬንገር የሚኖሯቸው አማራጮች ዳኒ ዌልቤክ እና የ 18 አመቱ ታዳጊ ኤዲ ኔኪትያህ ብቻ ይሆናሉ። 

ምክንያቱም የጥር ወር የክለቡ ክብረ ወሰን ሰባሪ አጥቂ ፒዬር ኤምሪክ ኦቦምያንግ በአውሮፓ መድረክ ለቀድሞ ክለቡ ዶርትሙንድ የተጫወተ በመሆኑ ለአርሰናል መሰለፍ የማይችል መሆኑ ነው።

ላካዜቲ ከኢሮፓ ሊግ የ 16ቱ ቡድኖች የደርሶ መልስ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ በተጨማሪ በካራቦአ ዋንጫ ፍፃሜ ከማንችስተር ሲቲ እንዲሁም ደግሞ በመጋቢት ወር ከሚደረጉ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ውጪ እንደሚሆን ተገምቷል።

Advertisements