የሴሪኣው ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ተከፋይ አሰልጣኝ ማነው?

​የጣሊያኑ ጋዜጣ የሆነው ጋዜታ ዴሎ ስፖርት በጣሊያን ሴሪኣ ከሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች ውስጥ ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ተከፋይ አሰልጣኞች ይፋ አድርጓል።

እንደ ተጫዋቾች ሁሉ አሰልጣኞችም የሚከፈላቸው ደሞዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ መጥቷል።

በተለይም በእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ ታላላቅ ቡድኖችን የሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች ከፍተኛ ተከፋይ ከሆኑት ውስጥ ይካተታሉ።

በጣሊያን ሴሪ ኣም ከሌሎች ሊጎች አንፃር በአንፃራዊነት የአሰልጣኞች ደሞዝ ዝቅ ያለ መሆኑን የሀገሪቱ ጋዜጣ የሆነው ጋዜታ ዴሎ ስፓርት ያወጣውን መረጃ ያስረዳል።

ጋዜጣው የሊጉ ከፍተኛ ተከፋይ የሆኑት የጁቬንቱሱ አሰልጣኝ የሆኑት ማሲሚሊያኖ አሌግሪ እንደሆኑ ሲገልፅ የሚያገኙትም አመታዊ 7 ሚሊየን ዩሮ ነው።

መልካም አጀማመር አድርገው እየቆዩ ወደ ታች መጓዛቸውን የቀጠሉት ኢንተርሚላኖችን እያሰለጠኑ የሚገኙት ሉቺያኖ ስፓሌቲ በአመት 3 ሚሊየን ዩሮ ያገኛሉ።

በኤሲ ሚላን ቪሴንዞ ሞንቴላን ተክቶ በሀላፊነት ላይ የወጣው ጄናሮ ጋቱሶ ደግሞ የሴሪኣው ዝቅተኛ ተከፋይ መሆኑን ጋዜጣው ያትታል።

ጋቱሶ በሚላን ታዳጊ ቡድን ውስጥ ያገኝ የነበረው በአመት 120ሺ ዩሮ ለውጥ ሳይደረግለት በዋና ቡድን ሀላፊነቱም የሚከፈለው ደሞዝ ነው።

የቬሮናው አሰልጣኝ ፋቪዬ ፔቺያ ደግሞ በአመት 250ሺ ዩሮ በማግኘት ከ 20ዎቹ የአሰልጣኞች ዝርዝር ውስጥ በ 19ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።

Advertisements