መልዕክት / ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከምሽቱ ተጠባቂ የቻምፕየንስ ሊግ ጨዋታ በፊት ለደጋፊዎች መልዕክት ላከ

እውነተኛ የፍፃሜ ጨዋታ የመሆን አቅም ያለው ከምሽቱ ተጠባቂው የማድሪድ እና የ ፒ ኤስ ጂ ጨዋታ በፊት ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለማድሪድ ደጋፊዎች መልዕክት ልኳል።

በላሊጋው ዋንጫ የማግኘት እድሉ የተሟጠጠው የአምናው አሸናፊ ሪያል ማድሪድ ከባርሴሎና በሰፊ ነጥብ ርቆ ተቀምጧል።

በስፔን ኮፓ ዴልሬም ማድሪዶች በጊዜ ከውድድሩ በመውጣታቸው አሁንም የውድድሩን የበላይነት ባላንጣቸው ባርሴሎናዎች ዘውዱን ሊደፉት በዋንጫ ጨዋታ ላይ ሲቪያን ብቻ መርታት ይጠበቅባቸዋል።

በነጮቹ ቤት በውድድር አመቱን ያለፉትን የቀውስ ወራቶች ለመርሳት የመጨረሻ አማራጫቸው ባለፉት ሁለት ተከታታይ አመታት ላይ አሸናፊ የሆኑበት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግን ለሶስተኛ ጊዜ ማንሳት ብቻ ይሆናል።

ይህ የማይሆን ከሆነ ግን የተለመደው የደጋፊዎች ተቃውሞ ተጠናክሮ መቀጠሉ አይቀርም።ውጤት ማጣቱ ደግሞ የክለቡ አሰልጣኝ ዜነዲን ዚዳንን እስከመቀየር ሊያደርስ እንደሚችል ይገመታል።

ይህን ሁሉ ለመቀየር ትልቅ አቅም ያለው በአውሮፓ ቻምፕየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ዛሬ ምሽት በበርናባው ማድሪዶች ሌላው የውድድሩ ከፍተኛ ግምት ከተሰጠው ፒ ኤስ ጂ ጋር ይፋጠጣሉ።

ሁለቱ ረብጣ ዶላሮችን ለተጫዋቾች በማውጣት የሚታወቁት በእግርኳሱ የከባድ ሚዛን ተፋላሚ ክለቦች የሚያመሳስላቸው ሌላው ነገር ዘንድሮ አጥብቀው የቻምፕየንስ ሊጉን ዋንጫ መፈለጋቸው ነው።

ሁለቱም የሚመኩባቸው ኮከብ ተጫዋቾች መያዛቸውም ሌላው ትኩረት ያገኘ ጉዳይ ሲሆን ማን ቡድኑን ወደ ቀጣዩ ዙር እንዲያልፍ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል የሚለውም በጉጉት የሚጠበቅ ሆኗል።

የጨዋታው አስፈላጊነት እና ጠንካራነት በመረዳትም ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለማድሪድ ደጋፊዎች መልእክቱን አስተላልፏል።

“እሮብ ከትልቅ ቡድን ጋር በጣም ጠንካራ ጨዋታ ይጠብቀናል።እኔ እና ቡድኑ እናንተን የምንጠይቀው ነገር እንደሁልጊዜው ሁሉ ያልተለመደ ድጋፋችሁን እንድትሰጡን ነው።ምክንያቱም አንድ ላይ ስንሆን በጣም ጠንካራ እንሆናለን።”ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

የሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ዛሬ ምሽት 4:45 በሳንቲያጎ በርናባው የሚደረግ ይሆናል።

Advertisements