“ሚሶት ኦዚል የአለማችን ምርጡ 10 ቁጥር ነው” – ሄነሪክ ሜክቴሪያን

Mesut Ozil is the best player in his position, says Henrikh Mkhitaryan

በጥር የዝውውር መስኮት ማንችስተር ዩናይትድን ለቆ  የሰሜን ለንደኑን ክለብ አርሰናልን የተቀላቀለው  ሄነሪክ ሜክቴሪያን ከወዲሁ የቡድን አጋሩን ሚሶት ኦዚልን አሞካሽቷል፡፡

የአርሰናልን የማጥቃት አቅም ለማስፋት የአሌክሲስ ሳንቼዝ የዝውውር አካል ሆኖ ኤሜሬትስን የረገጠው አርሜኒያዊው ኮከብ “ሚሶት ኦዚል የአለማችን ምርጡ 10 ቁጥር ነው” ሲል አወድሶታል፡፡

“ይህን ሁሉም ያውቃል ኦዚል አለማችን ላይ ካሉ ምርጥ ተጫዋቾች ውስጥ አንዱ ነው ፡፡ በእዚህ ቤት ተገኝቼም ከእርሱ ጋር በመጫወቴ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ እርሱ የድንቅ ክህሎት ባለቤት ነው፡፡ ” ሲል ስለ የቡድን አጋሩ ሚሶት ኦዚል ተናግሯል፡፡

ስለ አዲሱ የክለቡ ወዳጁ ፔየር ኤምሪክ ኦውባሚያንግም አስተያየቱን የሰጠው አርሜኒያዊው ኮከብ “በዚህ ክለብ ከኦውባ ጋር ዳግም መገናኘታችን አስደስቶኛል እርሱ ከሜዳ ውስጥም ከሜዳ ውጭም የኔ ምርጥ ወዳጅ ነው፡፡”

“ከእርሱ ጋር በጥምረት መጫወቴን እወደዋለው፡፡ በዶርትመንድ የነበረንን ጥሩ ጥምረት እዚህም እንደግመዋለን ብዮ አስባለው፡፡ የአርሰናል ደጋፊዎችም እርሱን በዚህ ክለብ መመለከታቸው እንደሚያሰደስታቸው ተስፋ አደርጋለው፡፡”

Advertisements