አከባበር / የእግር ኳሱ ዓለም ዝነኞች የፍቅር ቀን ውሎ

MAIN-BANNER

ሁሌም በፈረንጆቹ የካቲት 14 የሚደረገው የአለም የፍቅረኞች ቀን በትናንትናው ዕለትም ተከብሮ ሲውል ከዚህ ቀደም እንደነበረው የአለምን የእግር ኳስ ማህበረሰብ ጭምር ያሳተፈ ነበር፡፡ እኛም የአንዳንድ ክለቦች እና የእግር ኳሱ አለም ከዋክብታት የዕለቱን ውሎ አንደሚከተለው ተመልክተነዋል፡፡


ማንችስተር ዩናይትድን በቀዳሚነት ስናገኝ የኦልትራፎርዱ ክለብ የፍቅረኞች ቀንን በማስመልከት በአዲሱ ኮከቡ አሌክሲስ ሳንቼዝ ፎቶ ያሸበረቀና “በአለም ዙሪያ ላሉ ደጋፊዎች” የሚል መልዕክት የያዘን የኢንስታግራም መልዕክት አስተላልፏል፡፡

በሌላ በኩል ወደሰሜን ለንደን ስናመራ ግራኔት ዣካ አብራው ስምንት ወራትን ላስቆጠረችው ባለቤቱ ሊኦኒታ ሌካጅ “ፈገግታሽ ሀብቴ እና ሁሌም አብሮኝ እንዲቆይ የምፈልገው ነው፡፡” የሚል መልዕክትን በይፋዊ የማህበራዊ ገፁ በኩል አስተላልፎላታል፡፡

የቀድሞው የአንፊልድ ኮከብ ስቴቨን ዤራርድ በበኩሉ ቀለል ያለ የልብ ቅርፅ ምልክትን ካባለቤቱ አሌክስ ጋር የተነሳውን ምስል ጋር ከ “መልካም የፍቅረኞች ቀን ውዴ እጅግ በጣም አፈቅርሻለሁ፡፡” መልዕክት ጋር ለቋል፡፡

በአስገራሚ ሁኔታ ደግሞ የቀድሞው የዩናይትድ ዝነኛ ተከላካይ ጋሪ ኔቭል በአንድ ወቅት ለቀልድ የቀድሞ የቡድን አጋሩን ፖል ስኮልስን ሲስም የሚያሳይ የድሮ ምስል በመጠቀም ከእንኳን አደረሳችሁ መልክት ጋር በይፋዊ የትዊተር ገፁ ለቆ ታይቷል፡፡

የካታላኑ ባርሴሎና በበኩሉ አባላቱ የሚወዷቸው ነገሮች ናቸው ብሎ ያሰባቸውን እንደ እኩልነት፣ የቡድን ስራ፣ መከባበር፣ ጥረት፣ ጉጉት እና ባርሴሎና የሚለውን ቃል እራሱ በመጠቀም የመልካም የፍቅረኞች ቀን መልዕክት አስተላልፏል፡፡

Advertisements