ጂያንሉጂ ቡፎን ለተጨማሪ የውድድር ዘመን ስለመጫወት እያሰበ ነው

ጂያንሉጂ ቡፎን ለሌላ ተጨማሪ የውድድር ዘመን መጫወት ስለሚችልበት አማራጭ እና ስለወደፊት ዕጣ ፈንታው ከጁቬንቱሱ ፕሬዝዳንት አንድሪያ አንጀሊ ጋር እንደሚነጋገር ተናግሯል።

የ40 ዓመቱ ግብ ጠባቂ በመጪው ክረምት ከሚደረገው የዓለም ዋንጫው በኋላ እግርኳስ መጫወት ለማቆም ዝግጁ ነበር። ይሁን እንጂ ጣሊያን ለዓለም ዋንጫ ማለፍ ባለመቻሏ ቡፎን ጥሩ ስሜት እስከተሰማው ጊዜ ድረስ የተጫዋችነት ቆይታውን ለማራዘም በድጋሚ እንዲያስብበት አድርጎታል።

“ውሸት ልናገር ወይም የውሸት የሆነ ነገር እንዲጠበቅብኝ ላደርግ አልችልም።” ሲል በዚህ ሳምንት መጨረሻ ለስርጭት ለሚቀርበው የጣሊያኑ ስካይ ስፖርት ተናግሯል። ላ ጋዜጣ ዴሎ ስፖርት ደግሞ ይህ የቴሌቭዥን መሰናዶ ለአየር ከመብቃቱ በፊት ዘገባውን አስቀድሞ ለህትመት አብቅቶታል።

“እውነታው አሁንም የተከበረ ስምምነት ካለኝ ፕሬዝዳንቱ ጋር በመገናኘት ጠቃሚ የሆነ ውሳኔ ላይ የምንደርስ መሆኑ ነው።

“እነዚያ ቀናት [ከስዊዲን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የደረሶ መልስ ሽንፈት በኋላ የነበሩት] በጣም አስቸጋሪ ነበሩ። በዓለም ዋንጫው የተጫዋችነት ዘመኔን ማጠናቀቅ ፈልጌ ነበር። ምክኒያቱም የተጫዋችነት ዘመን ክብሬን ለማስታወስ የተመቸ ጊዜ ስለነበር ነው። እንዳለመታደል ሆኖ ያ አልተሳካም።” ሲል የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ጣሊያናዊው ግብ ጠባቂ ተናግሯል።

Advertisements