አቀባበል / የእንግሊዙ ክለብ አርሰናል ኡጋንዳን ሊጎበኝ መሆኑ ተገለፀ

የእንግሊዙ ክለብ አርሰናል በሰኔ 2019 ወደ አፍሪካዊቷ ሀገር ኡጋንዳ ለመምጣት ከሀገሪቱ የስፖርት ምክር ቤት ጋር ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

ካዎ ስፖርት የተሰኘው ድረገፅ የሀገሪቱን የስፖርት ምክር ቤት ሀላፊ ቦስኮ ኢንይክን ጠቅሶ እንደፃፈው ከሆነ ከስፖርት ቱሪዝም ጋር በተያያዘ ምክር ቤቱ ከኢምሬትሱ ክለብ ጋር ስምምነት ተፈራርሟል። 

እንደ ኢንይክን ገለፃ መድፈኞቹ የሀገሪቱን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞች እና የክሬንሶቹን ተጫዋቾች ወደ ሜዳቸው ኢምሬትስ በመጋበዝም የልምምድ መርሀ ግብር ሊያካሂዱላቸው መስማማታቸውም ተወስቷል። 

ምክር ቤቱ እንዳለው ከሆነ ከአርሰናል ጋር የፈፀመው ስምምነት ለሀገሪቱ እግር ኳስ እድገት እና ለስፖርት ቱሪዝም ገበያ መጠናከር ትልቅ ሚና እንዳለው ተያይዞ ተነግሯል።

ኡጋንዳ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ትልቅ የእግር ኳስ እመርታን ያሳየችና በአህጉሪቱ የእግር ኳስ መድረክ እንዲሁም በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጠንካራ ፉክክርን ማድረግ የቻለች ሀገር ናት።

Advertisements