የተረጋገጠ/ ጸጋዮ ኪዳነ ማሪያም  አዲሱ የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ

download

ባሳለፍነው ወር ከአሰልጣኝ ብርሀኔ ገ/እግዚያብሄር ጋር ተለያይቶ የነበረው ወልዋሎ አዲግራት የኒቨርስቲ ጸጋዮ ኪዳነ ማሪያምን አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙ እርግጥ ሆኗል፡፡

የታመኑ የኢትዮ አዲስ ስፖርት ምንጮች ከአዲግራት እንደተናገሩት ከሆነ ወልዋሎ አዲግራት የኒቨርስቲ እና የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ሀረር ቢራ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰልጣኝ ጸጋዮ ኪዳነ ማሪያም ለአንድ አመት በወልዋሎ የሚያቆያቸውን ስምምነት መፈራረማቸውን የተናገሩ ሲሆን አሰልጣኙም በክለቡ ቆይታቸው ወርሀዊ የ50 ሺ ብር ክፍያ እና እንዲሁም ለፊርማ 500 ሺ ብር እንደሚያገኙ የታመኑት ምንጮች ለኢትዮ አዲስ ተናግረዋል፡፡

አሰልጣኝ   ጸጋዮ ኪዳነ ማሪያም በያዝነው የውድድር አመት መጀመሪያ አርባምንጭ ከተማን በፕሪሚየር ሊጉ ያሰለጠኑ ሲሆን ባስመዘገቡት ደካማ የሚባል የሊግ ውጤትም አርባምንጭ ከተማ ከክለቡ እንዳሰናበታቸው የሚታወስ ሲሆን ከስንብታቸው ወራት በኋላም ፕሪሚየር ሊጉን በያዝነው አመት የተቀላቀለውን ወልዋሎ አዲግራት የኒቨርስቲን እስከ ቀጣዩ የውድድር አመት ድርስ የሚያሰለጥኑ ይሆናል፡፡

ከአሰልጣኝ ብርሀኔ ገ/እግዚያብሄር ስንብት በኋላ ሀብቶም ኪሮስ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲን በጊዜያዊነት ሲያሰለጥን የሰነበተ ሲሆን ክለቡም በ15 የፕሪሚየር ሊግ  ጨዋታዎች 16 ነጥቦችን ይዞ በ10ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ የቻለ ሲሆን ከ15 ጨዋታም ሶስቱን  ብቻ አሸንፎ በሰባቱ አቻ ወጥቶ በ5ቱ ተረትቶ በሊጉም 10 ግቦች አስቆጥሮ 18 ግቦችን አስተናግዷል፡፡

Advertisements