የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ተጋጣሚዎች ታወቁ

የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ተጋጣሚዎች ቅዳሜ ምሽት ይፋ ሲሆን ታላላቅ ቡድኖች የሚያገኟቸውን ቡድኖች አውቀዋል።

ከአርብ ጀምሮ የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታዎች እየተደረጉ የሚገኙ ሲሆን ወደ ሩብ ፍፃሜም ያለፉ ቡድኖች እየተለዩ ይገኛሉ።

ቼልሲ አርብ ለታ፣ዩናይትዶች ደግሞ ቅዳሜ ምሽት ያደረጓቸው ጨዋታዎች በማሸነፋቸው ወደ ሩብ ፍፃሜ መሸጋገራቸው አረጋግጠዋል።

ሲቲ እና ቶተንሀም ዛሬ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ሌሎቹ አላፊ ቡድኖች እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

ጨዋታዎቹ ከመጠናቀቃቸው በፊት በቀጣይ የሩብ ፍፃሜ እነማን ሊገናኙ ይችላሉ የሚለው ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል።

በድልድሉ መሰረት ትላልቅ ቡድኖች እርስበርስ የመገናኘት እድል የነበራቸው ቢሆንም ሳይገናኙ ቀርተዋል።

ሙሉ ድልድሉ

ሼፊልድ ዌንስዴይ/ስዋንሲ ከ ሮቻዳል/ስፐርስ

ዩናይትድ ከ ብራይተን

ሌሲስተር ከ ቼልሲ

ዊጋን/ማን ሲቲ ከ ሳውዝሀምፕተን 

በመጀመሪያ የተፃፉት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታቸውን በሜዳቸው ያደርጋሉ።

Advertisements