ማን ሲቲ ሳይታሰብ በዊጋን ተሸንፎ ከ ኤፍ ኤ ካፕ ውድድር ውጪ ሆነ

2013 ላይ በኤፍ ኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ማን ሲቲንን ማሸነፍ ችሎ የነበረው ዊጋን አትሌቲክ በዘንድሮው በአምስተኛው ዙር የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታ የፔፕ ጓርዲዮላውን ማን ሲቲን በድጋሚ ማሸነፍ ቻለ።

ምሽት በዲ ደብሊው ስታድየም የፕሪምየርሊጉ መሪ የፔፕ ጓርዲዮላው ማን ሲቲ ሳይታሰብ አስደንጋጭ ሽንፈት አጋጥሞታል።

ወደ ዲ ደብሊው ስታድየም አቅንቶ የአምስተኛው ዙር የኤፍ ኤ ካፕ መርሀ ግብር አከናውኖ ወደ ሩብ ፍፃሜ እንደሚቀላቀል ተገምቶ የነበረው ማን ሲቲ 1-0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

83% የኳስ ቁጥጥር የነበራቸው እንግዳዎቹ ጨዋታውን መቆጣጠር ቢችሉም ከእረፍት በፊት ፋቢያን ዴልፍ በቀይ ካርድ ወጥቶም እንኳን በተሻለ መንቀሳቀስ ችለው ነበር።

የዴልፍ በአጨቃጫቂ ሁኔታ መውጣት ፔፕ ጓርዲዮላን ጭምር ያስቆጣ እንደነበረ መመልከት ተችሏል።

የጨዋታው ብቸኛ ጎል የተገኘችው ከጨዋታ  መጠናቀቅ 11 ደቂቃ ቀደም ብሎ ሲሆን አግቢው ደግሞ ግሪግስ ነበር።

አጉዌሮ በጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ወደ ሜዳ ከገቡ የባለሜዳዎቹ ደጋፊዎች ጋር ግጭት የፈጠረ ሲሆን በቦክስ ሲማታም ታይቷል።

ዊጋን ዘንድሮ በዚህ ውድድር ዘንድሮ ሶስት የፕሪምየርሊግ ቡድኖችን ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በሩብ ፍፃሜው ደግሞ ሌላውን የፕሪምየርሊግ ተሳታፊ የሆነውን ሳውዝሀምፕተንን የሚገጥም ይሆናል።

በዚህም መሰረት ሲቲዎች በ 1999 ማን ዩናይትድ የሶስትዮሽ ዋንጫ (የቻምፕየንስ ሊግ፣ፕሪምየርሊግ እና የኤፍ ኤ ካፕ) ዋንጫ ያሸበፉበትን ታሪክ መስራት ባይችሉም አሁንም በሌሎቹ ወድድሮች እና በሊግ ካፕ ላይ ተሳታፊ በመሆናቸው በአመቱ መጨረሻ ከአንድ በላይ ዋንጫ የማግኘት እድሉ ሊፈጠርላቸው ይችላል።

Advertisements