ቼልሲ ከ ባርሴሎና | የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ቅድመ ቅኝት

ቼልሲ 16 ክለቦች በቀረቱ የየሻምፒዮንስ ሊጉ የደርሶ መልስ የመጀመሪያ ጨዋታ ማክሰኞ ምሽት በስታምፎርድ ብሪጅ ባርሴሎናን ይገጥማል።

በሃገሩ ውድድሮች ላይ የምንጊዜውንም ታላቅ ያለመሸነፍ ጉዞ እያደርገ የሚገኘውን እና የሻምፒዮንስ ሊጉን የምድብ ጨዋታውን በቀላሉ መወጣት የቻለው ባርሴሎና በአሁን ወቅት ካለው ብቃት አንፃር የአንቶኒዮ ኮንቴው ቡድን ለዚህ ጨዋታ ዝቅተኛ ግምት እንደሚሰተው ግልፅ ነው።


ወቅታዊ አቋም

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ባለፈው ወር በተከታታይ አምስት ጨዋታዎች ላይ አቻ ከተለያየ በኋላ ከካራባዎ ዋንጫ ውጪ በመሆን የ2018 ጅማሮው የተለየ ነበር። ከዚያ በኋላም በቦርንማውዝና ዋትፎርድ ከባድ ሽነፍቶች ገጥመውታል።

ይሁን እንጂ ባለፉት ሳምንታት በሜዳው ዌስትሃምን እና ኸል ሲቲን በቀላሉ በመርታ በአሁኑ ጊዜ የውጤት መንሸራተቱን መግታት ችሎ በፕሪሚየር ሊጉ ከመሪው ማንችስተር ሲቲ በአራት ደረጃዎች ዝቅ በማለት ተቀምጦ ይገኛል።

በአንፃሩ ባርሴሎና በላ ሊጋው በ24 ጨዋታዎች ላይ ባለመሸነፍ የውድድር ዘመኑን ክብረወሰን ጨብጦ በመጓዝ በቅርበት የሚከተለውን አትሌቲኮ ማድሪድን በሰባት ነጥቦች በቀዳሚነት በመምራት ላይ ይገኛል።

የካታላኑ ክለብ ባለፈው የውድድር ዘመን በሩብ ፍፃሜው በጁቬንቱስ ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ከሆነ ወዲህ ከ2015 የፍፃሜ የድል ዘመኑ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በፍፃሜ ላይ በመድረስ በተከታታይ ለሶስተኛ ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ ለማሸነፍ የሚፋለመውን ቀንደኛ ተቀናቃኙን ሪያል ማድሪድን የመግታት ተስፋ ሰንቆ ይህን ጨዋታ የሚያደረግ ይሆናል።

የቡድኖቹ ዜናዎች

ዴቪድ ልዊዝና ቲሞ ባካዮኮ የጉዳት ችግሮች ላይ የሚገኙ በመሆናቸው በማክሰኞ ምሽቱ ጨዋታ ላይ የመሰለፍ ዕድላቸው ጠባብ ነው። ሮዝ ባርክሌይ በመጀመሪያው የውድድር ዘመን ከሜዳ ካራቀው የቋንጃ ህመም ለማገግም አሁንም ጥረት እያደረገ የሚገኝ በመሆኑ ከላ ሊጋው መሪ ጋር በሚደረገው ጨዋታ ላይ የማይሰለፍ ይሆናል።

ኤርነስቶ ቫልቬርዴ ቶማስ ቨርማለን በዚህ ጨዋታ ላይ በመጀመሪያው አሰላለፍ ውስጥ ማካተታቸው አጠራጣሪ ከመሆኑ ውጪ ምንም አይነት አሳሳቢ የሆነ አዲስ የጉዳት እክል በቡድናቸው ውስጥ የለም።

ግምታዊ አሰላለፎች

ቼልሲ፡ ኮርቱዋ፣ አዝፒሊኩዌታ፣ ክርስቲያንሰን፣ ሩዲገር፣ ሞሰስ፣ ካንቴ፣ ፋብሪጋዝ፣ አሎንሶ፣ ዊሊያን፣ ሃዛርድ፣ ሞራታ

ባርሴሎና፡ ተር ሽቴገን፣ ሮቤርቶ፣ ፒኬ፣ ኡምቲቲ፣ አልባ፣ ፓውሊንሆ፣ ራኪቲች፣ ቡስኬት፣ ኢንየስታ፣ ስዋሬዝ፣ መሲ

ግምታዊ ውጤት

ቼልሲ አስቸጋሪ የውድድር ዘመን ጉዞ እያደረገ እንደመሆኑና ባርሴሎና ደግሞ በፊት ለፊቱ ላይ የበላይነት ያለው ክለብ እንደመሆኑ የማሸነፍ ምልክቱ በሙሉ ወደእንግዳው ቡድን የሚያጋደል ይመስላል። ይሁን እንጂ ከቀደሙ ታሪኮች አንፃር ሰማያዊዎቹ ከካታላኖውያኑ ጋር በሜዳቸው ለመጨረሻ ጊዜ ባደረጓቸው ሰባት ጨዋታዎች ላይ ያለመሸነፍ እና ሶስቱን የማሸነፍ እጅግ ጥሩ የሚባል የውጤት ክብረወሠን አላቸው።

ሊዮኔል መሲ በቼልሲ ላይ ፍፅሞ ግብ አስቆጥሮ የማያውቅ ሲሆን በ2012 የፍፁም ቅጣት ምት ስቷል።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ምንም እንኳ በለፉት የተወሰኑ ጨዋታዎች ላይ መሻሻል ቢያሳይም ይህ ጨዋታ ትክክለኛ ፈተና እንደሚሆንበት ይጠበቃል። ይህን በሚገባ ለመወጣትም ኃያል ብቃት ላይ የሚገኘውን ባርሴሎናን መግታት ይጠበቅበታል።

ግምታዊ ውጤት፡ ቼልሲ 1-1 ባርሴሎና

Advertisements