በአፍሪካ ቻምፕየንስ ሊግ የኢትዮጵያው ቅ/ጊዮርጊስ የዩጋንዳውን ኬሲሲኤን ይገጥማል

በ2018 የአፍሪካ ቻምፕየንስ ሊግ ቀጣይ የማጣሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያው ቅ/ጊዮርጊስ ከዩጋንዳው ሻምፕዮን ኬሲሲኤ ጋር ይጫወታል።

እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ቻምፕየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የዩጋንዳው ኬሲሲኤ ከማዳጋስካሩ ስናፕ ስፓርት ጋር 2-2 ቢለያዩም ከሜዳ ውጪ ባስቆጠረው ጎል ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።

በዩጋንዳ በተደረገው የዛሬው የመልስ ጨዋታ ባለሜዳዎቹ ማሸነፍ ብቻ አማራጭ አድርገው ቢጫወቱም ከተጋጣሚያቸው ጠንካራ ፉክክር ገጥሟቸዋል።

የጨዋታው ብቸኛ ጎልም የተገኘችው ከእረፍት መልስ 63ኛው ደቂቃ ላይ ሲሆን አግቢውም ፖል ሙኩሪዚ ነው።

ፖል ሙኩዙሪ

ብቸኛ ጎሉም ባለሜዳዎቹ ጨዋታውን በአጠቃላይ ውጤት 2-2  በማጠናቀቃቸው ከሳምንት በፊት ከሜዳቸው ውጪ ባስቆጠሩት ጎል ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችለዋል።

በዚህም መሰረት ኬሲሲኤ ወደ ቀጣዩ ዙር ቀደም ብሎ በፎርፌ ማለፉን ካረጋገጠው የኢትዮጵያው ተወካይ ቅ/ጊዮርጊስ ጋር በቀጣይ የሚጫወት ሲሆን የሁለቱ ቡድኖች አሸናፊ ወደ ምድብ ድልድሉ ይቀላቀላል።

ኬሲሲኤ ባለፈው አመት በተመሳሳይ በመጨረሻው የማጣሪያ ጨዋታ ላይ የ2016 የካፍ ቻምፕየንስ ሊግ አሸናፊ ሆኖ ከመጣው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር ተጫውቶ መሸነፉ ይታወሳል።

በወቅቱ ኬሲሲኤ ከሜዳው ውጪ 2-1 ተሸንፎ ቢመለስም በሜዳው ያደረገው የመልሱን ጨዋታ እስከ 83ኛው ደቂቃ ድረስ 1-0 መርቶ በመጨረሻም ላይቤሪያዊው አንቶኒ ላፎር ሰንዳውንስን የታደገውን የአቻ ጎል አስቆጥሮ ባለሜዳዎቹ ወደ ምድብ ድልድል ማለፍ ሳይችሉ ቀርተዋል። 

ቅ/ጊዮርጊስ በአንፃራዊነት ያጋጠመው ቡድን ጥሩ የሚባል ቢሆንም የዩጋንዳው ቡድን ባለፉት አመታት በውድድሩ ላይ እያሳየ ካለው መሻሻል አንፃር ፈረሰኞቹን መፈተን እንደሚችል መገመት አይከብድም።

የመጀመሪያ ጨዋታቸውንም በፈረንጆቹ መጋቢት 6(7) በአዲስ አበባ የመልሱን ደግሞ በካምፓላ የሚጫወቱ ይሆናል። 

Advertisements