ሚክሂታሪያን፣ እሱና ኦዚል በ10 ቁጥር ሚና በጋራ መጫወት እንደሚችሉ ገለፀ

ሄነሪክ ሚክሂታሪያን እሱ እና መሱት ኦዚል ምንም እንኳ ተመሳሳይነት ያላቸው ተጫዋቾች ቢሆኑም ነገር ግን በአርሰናል ቡድን ውስጥ በተመሳሳይ አጨዋወት መንገድ በጋራ በእንድ ላይ ሊጫወቱ እንደሚችሉ ገልፅዋል።


አርሰን ቬንገር መድኞቹ በቀደሙት ዓመታት እንደነበሯቸው ተጫዋቾች አይነት ሁልጊዜም የጨዋታ ፋጣሪ ተጫዋቾችን ይወዳሉ።

ቀደም ሲል በነበሯቸው ተጫዋቾች ላይም በጥር ወሩ የዝውውር መስኮት ተመሳሳይ ክህሎት ያለውን ሚክሂታሪያንን በአሌክሲ ሳንቼዝ ቅያሪ ከማችስተር ዩናይትድ በማስፈረም ወደክለባቸው አምጥተውታል።

አርመናዊው ተጫዋች አዲስ በተቀላቀለው የቡድኑ ስብስብ ውስጥ ብቃቱን አውጥቶ ለማሳየት ጥረት እያደረገ ቢገኝም ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ወደብቃቱ ሲመለስ አርሰናል “ሁለት 10 ቁጥር” ተጫዋቾችን በጋራ በማሰለፍ ተጠቃሚ ይሆናል ብሎ እንደሚያምን ገልፅዋል።

ሚኪታሪያን ከኦዚል ጋር አብሮ ስለመጫወት ለኢኤስፒኤን እንደተናገረው “አንዳድን ሰዎች በአንድ ላይ መጫወት እንደማንችል ይናገራሉ። ነገር ግን እነዚያ ሰዎች ያን ለምን እንደሚናጋሩ ሊገባኝ አይችልም።

“እኔ ከመሱት ጋር እየተጫወትኩ በመሆኔ እየተደሰትኩ ነው። እሱ በእጅጉ አስደናቂ እግርኳስ ተጫዋች ነው።

“ከእሱ ጋር መጫወቴ እንድሻሻል ያደርገኛል። ሁሉም ሰው የእሱን ክህሎትና ችሎት ያውቃል። ታዲያ ለምን አይሆንም? ሁሉም ነገር ይቻላል። በመሆኑም ለምን ሁለት 10 ቁጥሮች በሜዳ ላይ አይኖሩም?”

“በጣም በጥሩ ሁኔታ ብንጫወት እንኳ ሁልጊዜም የምንሻሻልበት ነገር እንደሚኖር ይታወቃል። የቱንም ያህል የማጥቃት አጨዋወት ብንከተል አሁንም መሻሻል እንችላለን።

“ምናልባትም በየትኛውም በኩል ልንሻሻል እንችላለን ማለቴ ነው። የቱንም ያህል በአንድ በኩል ጠንካራ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ደካማ ብንሆን ችግር የለውም። በርካታ የምንሻሻልባቸው ክፍተቶች ያሉ ግን ይመስለኛል።” ሲል ገልፅዋል።

በጆዞ ሞሪንሆ አሰልጣኝነት የመደበኛ ተሰላፊነት ሚናን በማጣት በኦልትራፎርድ ቆይታው አስቸጋሪ ጊዜያትን ያስለፈው ሚክሂታሪያን የልጅነት ህልሙ በነበረው አርሰናል የሚኖረውን ፋይዳ ለማስመስከርም ቁርጠኛ መሆኑን ገልፅዋል።

“አዎ ባለፉት ጊዜያት የአርሰናልን ጨዋታ ለብዙ ጊዜያት ስመለከት ነበር። በእርግጥም ቡድኑ በፕሪሚየር ሊጉና በሻምፒዮንስ ሊጉ ሲጫወት ተመልክቼዋለሁ።” በማለት “እንዲሁም አርሰን ቬንገር ክህሎት ያላቸው ወጣት ተጫዋቾችን እንዴት እንደሚጠቀም እና አብሯቸው እንደሚሰራም ተመልክቻለሁ።” ሲል አክሎ ተናግሯል።

Advertisements