መሲና ስዋሬዝ በዚህ የውድድር ዘመን ከ74 የአውሮፓ ክለቦች በላይ ግብ ማስቆጠር ችለዋል

ሁለቱ የባርሴሎና የአጥቂዎች፣ ሊዮኔል መሲና እና ልዊስ ስዋሬዝ በዚህ የውድድር ዘመን በጋራ ያስቆጠሯቸው 42 ግቦች 74 የአውሮፓ ክለቦች ካስቆጠሯቸው ግቦች የሚበልጥ ነው።

በዚህ የውድድር ዘመን አርጄንቲናዊው 22 ጊዜ፣ ኡራጓዊው ደግሞ 20 ጊዜ ኳስና መረብን ማገናኘት ችለዋል።

ይህ ሁለቱ የፊት ተጫዋቾች ያስቆጠሩት ድምር ግብም በአውሮፓ አምስት አበይት ሊጎች ላይ የሚገኙ 74 ክለቦች ካስቆጠሩት ግብ የሚልቅ ነው።

በላ ሊጋው በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አትሌቲኮ ማድሪድ ያስቆጠሯቸው ግቦች 41 ሲሆኑ፣ ይህም ከሁለቱ የፊት ተጫዋቾች በአንድ ግብ ያነሰ ነው።

ሁለቱ ተጫዋቾች ካስቆጠሯቸው 42 ግቦች የበለጠ ግቦችን ያስቆጠሩት አምስት የላ ሊጋ ክለቦች ብቻ ናቸው። እነሱም ሪያል ማድሪድ፣ ሪያል ቤቲ፣ ሴልታ ቪጎ፣ ቫሌንሺያና ሪያል ሶሴዳድ ናቸው።

በሌላ በኩል ከመሲ እና ከስዋሬዝ በላይ የሆኑ ግቦችን ማስቆጠር የቻሉ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ደግሞ ማንችስተር ሲቲ፣ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ሊቨርፑል፣ ቼልሲ፣ ቶተንሃምና አርሰናል ብቻ ናቸው።

ሁለቱ ተጫዋቾች ተጨማሪ ግቦችን ሊያስቆጥሩበት የሚችሉበት ጨዋታ ሃሙስ ምሽት በባርሴሎና እና ባላስ ፓልማስ መካከል ይደረጋል።

Advertisements