አርሰናል ከ ማንችስተር ሲቲ ፡ የጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

ሁለቱ ክለቦች እሁድ አመሻሹ ላይ ካደረጉት የካራባዎ ካፕ ጨዋታ በኋላ በአምስት ቀናት ልዩናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በፕሪሚፐር ሊጉ ዛሬ (ሃሙስ) ምሽት በኤመራትስ ይገናኛሉ።

የሁለቱ ክለቦች የከዚህ በፊት ግንኙነት

ሁለቱ ክለቦች ከዚህ ቀድመም ለመጨረሻ ጊዜ በፕሪሚየር ሊጉ የተገናኙት ባለፈው ህዳር ወር ነበር። በዚህ ጨዋታም ኬቨን ደ ብሩይኔ፣ ሰርጂዮ አጉዌሮ እና ጋብሬል ኼሱስ ባስቆጠሩት ግብ ሲቲ 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸናፊ መሆን ችሏል። የአርሰናልን ብቸኛ ግብ ያስቆጠረው ደግሞ አሌክሳንደር ላካዜቲ ነበር።

ቁልፍ ፍልሚያ

ሰርጂዮ አጉዌሮ ከ ሽኮድራን ሙስታፊ

ሰርጂዮ አጉዌሮ በዚህ የውድድር ዘመን ባስቆጠራቸው 21 የፕሪሚየር ሊጉ ግቦች የማን ሲቲ ኃያል ተጫዋች ከመሆኑም ባሻገር ከአርሰናል በተደረጉ ጨዋታዎች ላይም ልዩ የሆነ ብቃት በማሳየት ይታወቃል።

አግዌሮ በዚህ የውድድር ዘመን በሰሜን ለንደኑ ክለብ ላይ ሁለት ግቦችን በስሙ ማስመዝገቡ ብቻ ሳይሆን ክለቡ ከመድፈኞቹ ጋር ባደረጋቸው ያለፉት እንዳንዱ አምስት ጨዋታዎች ላይም ፍብ ማስቆጠር ችሏል።

ሙስታፊ የሲቲውን አስቸጋሪ አጥቂ ለማቆም በከራባኦ ካፕ ጨዋታ ላይ የሰራቸውን ስህተቶች ማረም ይጠበቅበታል። ትኩረቱን ሰብስቦ በጥንቃቄ የማይጫወት ከሆነ ግን የሚጠብቀው ከባድ ነገር ይሆናል።

የቡድን ዜናዎች

አርሰናል በዚህ ጨዋታ ላይ ናቾ ሞንሪልን በጀርባ ጉዳት፣ አሌክሳንደር ላካዜቲን በጉልበት ጉዳት እና ሳንቲ ካዛሮላን በተረከዝ ጉዳት በዚህ ጨዋታ ላይ አያሰልፍም።

በአንፃሩ ባለፈው የካራባኦ ካፕ ጨዋታ ላይ የቋንጃ ጉዳት የገጠመውን ፈርናንዲንሆን፣ እንዲሁም ለረጅም ጊዜያት በጉዳት ላይ የሚገኘውን ቤንጃሚ ሜንዲን የማያሰልፍ መሆኑ እርግጥ ሲሆን፣ ራሂም ስተርሊንግም በዚህ ጨዋታ ላይ መሰለፉ የሚያጠራጥር ቢሆንም ቢያንስ ግን በተቀያሪ ወንበር ላይ እንደሚኖር ይጠበቃል።

ግምታዊ አሰላለፍ

ሁለቱም ክለቦች የፊታችን እሁድ ጨዋታ የሚኖራቸው መሆኑ በዛሬ ምሽቱ አሳላለፍ ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ ይኖራል። በተለይም የሲቲ ቀጣይ ጨዋታ ከቼሊ ጋር በመሆኑ የአላለፍ ለውጥ እንደሚኖር ይጠበቃል። ይሁን እንጂ የምሽቱ ጨዋታም ወሳኝ እንደመሆኑ ሁለቱም ክለቦች ጠንካራ አሰላለፍ እንደሚጠበቁ ይገመታል።

የአርሰናል ግምታዊ የመጀመሪያ አሰላለፍ፡ ቼክ፣ ቻምበርስ፣ ሙስታፊ፣ ኮሸልኒ፣ ቤለሪን፣ ዣካ፣ ዊልሼር፣ ኮላሲናች፣ ኦዚል፣ ሚክሂታሪያን፣ አውባምያንግ

የማንችስተር ሲቲ ግምታዊ የመጀመሪያ አሰላለፍ፡ ኤደርሰን፣ ዎከር፣ ኮምፓኒ፣ ላፖርቴ፣ ዳኒሎ፣ ጉንዶጋን፣ ደ ብሩይኔ፣ ዴ. ሲልቫ፣ ሳኔ፣ በ. ሲልቫ፣ አጉዌሮ

ግምቶች

በዚህ የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ ላይም ሆነ በካራባዎ ካፕ በአርሰናል ላይ ከወሰዱት የበላይነት አንፃር ሲቲ ይህን ጨዋታ አያሸንፍም ብሎ መከራከሪያ ናጥብ ማቅረብ ይቸግራል።

ይሁን እንጂ የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ከዚህ ጨዋታ ሶስት ቀናት ልዩነት በኋላ ሌላ ከባድ ጨዋታ የሚጠብቀው እንደመሆኑ የሚጠቀመው አሰላለፍ የዚህን ጨዋታ ውጤት ሊቀይረው እንደሚችል እና አርሰናልም ይህን ዕድል እንደሚጠበቅበት መገመት አይከብድም። ነገር ግን ሲቲ ከላይ በግምት የተቀመጠው አሰላለፍ ይዞ የሚገባ ከሆነ ጨዋታው አርሰናል 1-2 ማንችስተር ሲቲ።

Advertisements