በምሽቱ የአርሰናል አቋም የተበሳጨው ግብፃዊ የክለቡ ደጋፊ የስታድየም ወጪውን አርሴን ዌንገር እንዲተኩለት ጠየቀ

መድፈኞቹ ማን ሲቲን አስተናግደው በተሸነፉበት የትናንቱ ምሽት ጨዋታን ለመመልከት ከግብፅ ወደ እንግሊዝ አቅንቶ በኤምሬትስ የታደመው ግብፃዊ የአርሰናል ደጋፊ ከጨዋታው በኋላ የስታድየም መግቢያ ወጪውን አርሰን ዌንገር እንዲተኩለት ጠይቋል።

አርሰናሎች ትናንት ምሽት ያደረጉት የፕሪምየርሊግ ጨዋታ በሜዳቸው አስደንጋጭ ሽንፈት አስተናግደዋል።

ጨዋታው በመጀመሪያ ግማሽ በተቆጠሩ ሶስት ጎሎች ሲቲዎች መድፈኞቹን በደርሶ መልስ ጨዋታ በማሸነፍ ከአርሰናል 6 ነጥብ ማግኘት ችለዋል።

አርሰናሎች ከሶስት ቀናት በፊትም በካራባኦ ካፕ የዋንጫ ጨዋታ በተመሳሳይ 3 – 0 የተሸነፉ በመሆኑ በአጠቃላይ በሲቲዎች በውድድር አመቱ ሶስተኛ ሽንፈታቸውን ቀምሰዋል።

የምሽቱን ጨዋታ ለመመልከት ከግብፅ ወደ እንግሊዝ አቅንቶ በኤምሬትስ ስታድየም የታደመው የክለቡ ደጋፊ በቡድኑ አቋም ተበሳጭቶ ስታድየሙን ለቋል።

ከጨዋታው በኋላ ከክለቡ የቴሌቭዥን ጣቢያ ጋር ቆይታ ያደረገው ግብፃዊው ደጋፊ በብስጭት አርሴን ዌንገር ለስታድየም መግቢያ ያወጣውን ወጪ እንዲተኩለት ጠይቋል።

አርሰናል በፕሪምየርሊጉ ካሉ ክለቦች ከፍተኛ የስታድየም የመግቢያ ክፍያ ከሚያስከፍሉ ውስጥ የሚካተት ሲሆን ይኸው ግብፃዊው ስታድየም ለመግባት ብቻ 2360 የግብፅ ፓውንድ ወጪ አድርጓል።

ይህ ጨዋታ በእውነቱ በኤምሬትስ ተገኝቼ የተመለከትኩት የመጀመሪያ ጨዋታዬ ነው።ነገርግን የከፈልኩትን አርሰን ዌንገር እንዲተኩልኝ እጠይቃለው።ከግብፅ የመጣሁት ይህን ጨዋታ ለመመልከት ነበር፣ነገርግን ጨዋታው በጣም አሳዛኝ ነበር።”

ምን የተፈጠረ ነገር አለ? ተብሎ ተከታይ ጥያቄ የቀረበለት ግብፃዊው የመድፈኞቹ ደጋፊ “ምን ጥሩ ነገር ነበር?ዌንገር ውጣ! እሱ የሰራውን ጥሩ ነገር እያበላሸ ነው

“በጨዋታው ሶስት ተጫዋቾች 90 ደቂቃ ሙሉ ሲያሟሙቁ ነበር።ነገርግን ምንም አይነት ቅያሬ አልተደረገም።ይህ ምን ማለት ነው?

“እስከዛሬ ድረስ የሰራውን አከብርለታለው ነገርግን አሁን እየሰራው ያለው ነገር የማከብረው ነገር የለኝም።እሱ ለክለቡ ክብር ካለው መልቀቅ አለበት።” ሲል ግብፃዊ   ደጋፊ በንዴት ሀሳቡን ሰጥቷል።

አርሰናሎች ከመሪው ሲቲ በ 30 ነጥብ የራቁ ሲሆን አራተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው የከተማቸው ተቀናቃኝ ቶተንሀሞች ደግሞ በአስር ነጥብ ርቀው ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

በቀጣይም በፕሪምየርሊጉ ብራይተንን የሚገጥሙ ሲሆን በዩሮፓ ሊግ ደግሞ ከ ኤሲ ሚላን ጋር ጠንካራ ጨዋታ ይጠብቃቸዋል።


Advertisements