ውድድር/ በ7ኛው የህዳሴ ዋንጫ 4 ክለቦች ተካፋይ ይሆናሉ

የታላቁ ህዳሴ ግንባታን መሰረት ድንጋይ መጣል ተከትሎ የሚካሄደው 7ኛው የህዳሴ ዋንጫ ውድድር በዚህ አመት ሲቀጥል 4 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡

ከየካቲት29 እስከ መጋቢት 2 ድረስ በሚካሄደው ውድድርም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን በ29 ነጥቦች የሚመራውን ደደቢትን ጨምሮ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮኤሌክትሪክ ይካፈላሉ፡፡

በአዲስ አበባ ስቴዲየም በሚካሄደው በዚህ የግማሽ ፍታሜ ውድደርም የካቲት 29 ሀሙስ ደደቢት ከ ሲዳማ ቡና በ9 ሰዓት ሲገናኙ በ11 ሰዓት ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

የህዳሴ ግድቡ የፍጻሜ ጨዋታ እሁድ መጋቢት 2 አዲስ አበባ ስቴዲየም ሲቀጥል በ8 ሰዓት የደረጃ እንዲሁም በ10 ሰዓት ደግሞ የደረጃ ጨዋታ የሚደረግ ይሆናል፡፡

Advertisements