በርሚንግሀም 2018 / ገንዘቤ ዲባባ ዛሬ ምሽት 1500 ሜትር የፍጻሜ ውድድር ታደርጋለች

28377869_1611003702281794_4382764366330686142_n

ዛሬ 3ኛ ቀኑን  በያዘው የአለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ለሁለተኛ የወርቅ ሜዳልያ በ1500 ሜትር የፍጻሜ ውድድሯን ታደርጋች፡፡

ትላንት ምሽት በተካሄደ የሴቶች 1,500 ሜ. ማጣሪያ ላይ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ 4፡06.25 በሆነ ጊዜ ከምድቧ ቀዳሚ ሆና ወደ ፍጻሜው ያለፈች ሲሆን ዛሬ ምሽት 5፡39 ተጠባቂውን የፍጻሜ ውድድር የምታደርግ ይሆናል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በበርሚንገሀም አሬና በሚደረገው በዚህ የማጣሪያ ውድድርም ኢትዮጵያን በመወከል አማን ወጤ እና ሳመኤል ተፈራ ቀን 8፡15 ላይ የማጣሪያ ውድድራቸውን የሚያደርጉ ሲሆን ማጣሪያውን የሚያልፉ ከሆነምነገ ምሽት ለሚደረገው የፍጻሜ ውድድር ማለፋቸውን የሚያረጋግጡ ይሆናል፡፡

Advertisements