በአለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ገንዘቤ ዲባባ ሁለተኛ ወርቅ ለኢትዮጵያ አስገኘች

በበርሚንግሃም እየተካሄደ ባለው የአለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እየተሳተፈ ያለው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን በገንዘቤ ዲባባ አማካኝነት ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳልያ አሳክቷል፡፡

ምሽቱን በተካሄደው የ1500 ሜትር ውድድር በማሸነፍ በአጠቃላይ በአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የውድድር ታሪኳ አምስተኛ የሆነውን የወርቅ ሜዳልያ የግሏ ማድረግ ችላለች።

ገንዘቤ ከትናንት በስተያ የተደረገውን የ3,000 ሜትር ውድድር በማሸነፍ ለሶስተኛ ጊዜ የርቀቱን አሸናፊነት አግኝታ የመሰረት ደፋርንና የጋብሬላ ዛቦን ክብረ ወሰን ተጋርታለች።

አትሌቷ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 4:05:27 የፈጀባት ሲሆን እሷን በመከተል ላውራ ሙይርና ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፈን ሃሰን ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነው በመግባት የሜዳልያ ገበታው ተቋዳሽ ሆነዋል፡፡

Advertisements