አሳዛኝ / የፊዮረንቲናው አምበል ዴቪድ አስቶሪ ድንገተኛ ሞት ምክንያት የሚላን ደርቢ ተራዘመ

የፊዮረንቲናው አምበል ጣሊያናዊው ዴቪድ አስቶሪ በሆቴሉ ውስጥ ሞቶ በመገኘቱ ደርቢ ዴላ ማዶኒናን ጨምሮ ዛሬ ሊካሄዱ የነበሩት የሴሪኣ ጨዋታዎች ተራዘሙ።

ጣሊያናዊው የ 31 አመቱ የፊዮረንቲናው አምበል የሆነው ዴቪድ አስቶሪ ዩዲኒዜን ከመግጠማቸው በፊት በሆቴል ውስጥ በተኛበት ህይወቱ ማለፉ መላውን የእግር ኳስ ወዳጆችን አስደንግጧል።

የክለብ ጓደኞቹ ጠዋት ተጫዋቹ ለቁርስ ባለመገኘቱ እና ስልክም ባለማንሳቱ የሆቴሉን በር ሰብረው ከገቡ በኋላ ባዩት ነገር ማመን አልቻሉም።

ክለቡ በመግለጫው የተጫዋቹን ህይወት ማለፍ ካሳወቀ በኋላ ዜናው በመላው አለም መነጋገሪያ ሆኗል።

የተጫዋቹ ህይወት ማለፍ በግልፅ ምክንያቱ ባይታወቅም አንዳንድ መረጃዎች ግን ተጫዋቹ ህይወቱ ያለፈው በልብ ህመም እንደሆነ እየገለፁ ይገኛሉ።

በዚህም መሰረት ዛሬ ምሽት በጉጉት እየተጠበቀ ያለው የደርቢ ዴላ ማዶኒናን ጨምሮ በሴሪኣ ዛሬ ሊደረጉ ፕሮግራም የተያዘላቸው ጨዋታዎች በሙሉ ለሌላ ጊዜ ተላልፈዋል።

አስቶሪ 2011 ላይ ለጣሊያን ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታውን ካደረገ በኋላ በአጠቃላይ 14 ጨዋታዎችን መጫወት ችሏል።

የጨዋታ ጊዜውን 2006 ላይ በሚላን ቢጀምርም በክለቡ የሁለት አመት ቆይታ በሴሪ ኣው ላይ ሚላንን ወክሎ ባለመሰለፉ በውሰት ለሌላ ክለብ በውሰት ተሰጥቶ ነበር።

Advertisements