“በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ለመሳተፍ የኢሮፓ ሊግ ውድድር አቋራጭ ነው” አርሰን ዌንገር

ፅሁፍ ዝግጅት :  በመንሀጁል ሀያቲ

መድፈኞቹ ከ2002 በሆላ ለመጀመሪያ ጊዜ በተከታታይ ለ4ተኛ ጊዜ ሽንፈትን አስተናግደዋል፡፡ አርሰን ዌንገር ከሽንፈቱ በኋላ አስተያታቸውን ሰጥተዋል፡፡  

ብራይተንን ከሜዳቸው ውጭ የገጠሙት መድፈኞቹ ፤ በባለሜዳዋቹ ብራይተኖች የ 2 ለ 1 የሽንፈት ፅዋን ተጎናፅፈው ለመመለስ ተገደዋል፤ የብራይተኑ የሽንፈት ውጤት ለአርሰናሎች ለተከታታይ 4ተኛ ጊዜ ሽንፈት ሁኖ ተመዝግቧል ይሄም ከ2002 በሆላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆኗል፡፡

የአርሴናል ቤት የአሰልጣኝነት ስራቸውን ለማስጠበቅ እየከበዳቸው ያሉት እና ጫናው የበዛባቸው አርሴን ቬንገር ስለቀጣዬ አመት የሻምፒዬንስ ሊግ ተሳትፎ እና ስለ ሽንፈቱ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። “ተመልከቱ ተስፋ መቁረጡ ይገባኛል ፤ ከባለፈው ሳምንት ከደረሰብን ነገር ቶሎ ለማገገም በጣም ከባድ ነው፤ በጣም በከባድ ጊዜ ውስጥ እየተጓዝ ነው ያለነው.” .

” ከእውነት ያልራቀ ልንሆን ይገባል፤ በሻምፒዬንስ ሊጉ ለመሳተፍ የሁለት ቡድኖችን መውደቅ ያስፈልገናል ፤ ነገር ግን ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ በሆላ ብዙ ነጥቦችን ይጥላሉ ብሎ ማሰብ ከባድ ነው ፤ ነገር ግን የተቻለንን ሁሉ በማድረግ ሩቅ መጓዝ ይኖርብንል ለዚህ ደግሞ የአውሮፖ ሊጉ ውድድር ተመራጩ መንገድ ነው.

” . አርሴናል ከብራይተኑ ሽንፈት በሆላ በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 6ተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል ፤ የቀጣይ አመት የሻምፒዬንስ ሊግ ተሳትፏቸውም ጥያቄ ውስጥ ገብቷል ወይስ አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር ያለፈው አመት የጆዜ ሞሪንሆን የሻምፒዬንስ ሊግ የመሳተፊያ መንገድ በኢሮፖ ሊግ በማድረግ ይሳካላቸው ይሆን?

 

 

 

 

 

 

Advertisements