የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን

ማንችስተር ሲቲ ፕሪሚየር ሊጉን በ18 ነጥቦች ልዩነት በቀዳሚነት በመምራት የዋንጫ ክብርን የመቀዳጀት የተስፋ ጉዞውን አጠናክሮ በቀጠለበት የሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ የመውጣትና የመውረድ የውጤት ለውጥ ያሳዩ ቀልብ ሳቢ ጨዋታዎችን አስመልክተውናል

በዚሁ መሰረት በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ለቡድናቸው ስኬት የበኩላቸውን ብቃት ያሳዩ 11 ተጫዋቾች እና አንድ አሰልጣኝ የተካተቱበትን ምርጥ ቡድን እንደሚከተለው ተመለከትነዋል።

ጃክ በትላንድ

ባለፈው ሳምንት ያሳየውን መጥፎ የሚባል ብቃት በማሻሻል ስቶክ ሲቲ የተቃጣበትን ሶስት ወሳኝ የሚባሉ የግብ ሙከራዎችን በማምከን ከሜዳው ውጪ ከሳውዛምፕተን ጋር ነጥብ ተጋርተው መውጣት እንዲችሉ አድርጓል። ይህ ብቃቱም ለእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሰልጠኙ ጋርዝ ሳውዝጌት እፎይታ የሚሰጥ ይሆናል።

ማት ላውተን

ኤቨርተን ከመመራት ተነስቶ ወደአሸናፊነት እንዲመለስ ለማድረግ ታላቅ ፍልሚያ አድርጓል። አሽሊ ባርነስ ላስቆጠረው ግብ በተጫዋቾ መኃል ኳስን ሰንጥቆ በማመቻቸ እና ወደፊት ሄዶ መጫወት በመቻል እስደናቂ ብቃቱንም ማሳየትም ችሏል።

ቪርጅል ቫን ዳይክ

ከኒውካሰል ዩናይትድ ጋር ያደረገው ጨዋታ በጣም ፈተኝ ነበር ለማለት ቢቸግርም፣ ነገር ግን ቫንዳይክ በተለይም በአየር ላይ ኳስ ብልጫ ነበረው። በሊቨርፑል የተከላካይ ክፍል ላይ ዳግመኛ መረጋጋትን መፍጠርም ችሏል።

ሌዊስ ደንክ

ብራይተን አርሰናልን ባሸነፈበት ጨዋታ በቀኝ የግቡ መረብ በኩል የመጀመሪያውን ግብ ማስቆጠር ችሏል። ተጫዋቹ በመላው የውድድር ዘመን ድንቅ የሆነ ብቃት የነበረው ሲሆን በመስመር ላይ በነበረው አጨዋወትም የአርሰን ቬንገረን ቡድን በዚያ ስፍራ ላይ ደከማ እንዲሆን ምክኒያት ነበር።

አሌክስ ኦክስሌድ-ቻምበርሌን

ኦክስሌድ-ቻምበርሌን ሊቨርፑል በኒውካሰል ላይ የመጀመሪያዋን ግብ ሲያስቆጥር ያሳየው ኃይለኛ፣ አዎንታዊና በብልሃት ቆርጦ የመግባት አጨዋወት አይነት ይኖረዋል ተብሎ በብዙዎች ዘንድ ተስፋ የሚያደረግበት ተጫዋች ነው። ለአርሰናልም ሌላኛው የወቀሳ ምንጭ ነበር።

ኪ ሱንግ-ዩንግ

ኪ ለስዋንሲ አሸናፊነት ያሳየው ብቃት በጥር የዝውውር መስኮት ወቅት ሊያስፈርሙት ሙከራ አድርገው በነበሩት ተሸናፊዎቹ ዌስት ሃሞች ላይ ጉዳት የሚያደርስ ነበር። የመጀመሪያዋንም ግብ ያስቆጠረውም እሱ ነበር።

ፓስካል ግሮስ

የጀርመናዊው ግዢ የውድድር ዘመኑ ቅናሽ የሚባል ግዢ ነበር። ብራይተኖች እሱን ባላሰለፉባቸው ጨዋታዎች ማስቆጠር የቻሉት አንድ ግብ ብቻ ሲሆን፣ ግሌን ሙራይ በእስደናቂ ሁኔታ በጭንቅላት ገጭቶ እንዲያስቆጥር ያስቻለውን ወሳኝ የማሸነፊያ ግብ በማሻገር ያመቻቸውም እሱ ነበር።

ሊሮይ ሳኔ

የሲቲው የፊት ተጫዋች ባለፉት ጨዋታዎች ላይ ያሳየው ፍጥነትና ኳስን በሚገባ ተቆጣጥሮ የመሮጥ ችሎታው አስደናቂ ነበር። አሁንም ቼልሲ ላይ ይህንኑ መድገም ከመቻሉም ባሻገር ባይሳካለትም የውድድር ዘመኑ ምርጥ ግብ ሊሆን የሚችል የግብ ሙከራ ማድረግም ችሏል።

ሁንግ-ሚን ሶን

ሶን ያስቆጠራቸው ሁለት ተጨማሪ ግቦች በውድድር ዘመኑ በፕሪሚየር ሊጉ ላይ ያስቆጠረቸውን ግቦች 10 አድርሶለታል። በጠቃላይ ውድድሮች ላይም ያስቆጠራቸው 15 ግቦች ለቡድን አጋሮቹ የግብ ዕድሎችን በማመቻቸት ለሚታወቀው ተጫዋች ድንቅ የሚባሉ ናቸው።

ትሮይ ዲኒ

ዲኒ ዋትፎርድ አሸናፊ እንዲሆን አሁንም አስደናቂ ግብ ማስቆጠር ችሏል። ይህ ደግሞ በጥር ወር ሊያስፈርሙት ሙከራ አድርገው ለነበሩት ዌስት ብሮሞች የሚያስቆጭ ነገር ነበር።

አንድሬ አየው

ጋናዊው ተጫዋች ዌስት ሃምን በመተው በማለት ዳግመኛ ወደስዋንሲ መመለስን መርጧል። ይህ ደግሞ የዴቪድ ሞየሱን ቡድን በእጅጉ የሚያሳምም ጉዳይ ነበር። አየው በዚህ ጨዋታ ላይም ስዋንሲ ነጥብ ይዞ እንዲወጣ ትልቁን ሚና የተጫወተ ተጫዋች ነበር።

አሰልጣኝ: ክሪስ ሂዩተን

ብራይተን ክለቦች እንደክለብ ራሳቸውን እንዴት ወደፊት ማሸጋገር እንዳለባቸው ለማሳየት ምሳሌ የሚሆን ክለብ ነው። የክለቡ ባለቤት ቶኒ ብሉም ለክለቡ እድገት ከፍተኛ የመዋዕለ ንዋይ ፈሰስ አድርገዋል። በመሆኑም ብራይተኖች በሁለት እግራቸው መቆም የሚጠበቅባቸው ጉዳይ ነበር። በመሆኑም የሽግግራቸው መዋቅራ አስደናቂ ነው። ክለቡ በመለወጥ ላይም ይገኛል። ለዚህ ለውጥ ደግሞ ተገቢው ምስጋና ሊቸረው የሚገባው አስልጣኛቸው ክሪስ ሂውተን ነው። ሂዩተን ብዙውን ጊዜ በፕሪሚየር ሊጉ ካለው ብቃት በታች ዝቅተኛ ግምት ሲሰጠው የቆየ አሰልጠኝ ነበር። ይሁን እንጂ አሰልጠኙ ጨርሶ ዝቅተኛ ግምት ሊሰጠው እንደማይገባ ያለማቋረጥ እያሳየ ይገኛል።

Advertisements