Skip to content
Advertisements

ኤዲን ዜኮ የአለማችን የመጀመሪያው ተጫዋች የሚያደርገውን ታሪክ አስመዘገበ

ግዙፉ ቦስንያዊ የሮማ የፊት አጥቂ ኤደን ዜኮ ከአለማችን አምስቱ ታላላቅ ሊጎች በሶስቱ ላይ አምሳ እና ከዚያ በላይ ጎል ማስቆጠር የቻለ የመጀመሪያው ተጫዋች የሚያደርገውን ታሪክ ሰርቷል፡፡

ትናንት ምሽት የሴሪ አውን መሪ ናፖሊ 4-2 በሆነ ውጤት ያሸነፉት ሮማዎች ከአራቱ ጎሎች መካከል ሁለቱን በቀድሞው የማንችስተር ሲቲ አጥቂ ዜኮ አማካኝነት ያስመዘገቡ ሲሆን እነዚህ ሁለት ጎሎችም ዜኮ በሴሪያው ያስቆጠራቸው 49 እና 59ኛ ጎሎች ሆነው ተመዝግበውለታል፡፡

አምስቱ የአለማችን ታላላቅ ሊጎች የሚባሉት(እንግሊዝ ፣ ስፔን ፣ ጣልያን ፣ ጀርመንና ፈረንሳይ) ውስጥ በሶስቱ ቆይታ የነበረው ዜኮ በየሄደበት የተረጋገጠለት ጎል አስቆጣሪ መሆኑን ማሳየቱን የቀጠለ ሲሆን ይህም ለአዲስ ክብር አብቅቶታል፡፡
ዜኮ በጀርመን ቆይታው ለዎልፍስበርግ 66 ጎሎችን ማስቆጠርና ክለቡንም ለቡንደስሊጋ ክብር ማብቃት ከቻለ በኋላ ወደእንግሊዝ በመምጣት ማንችስተር ሲቲን ተቀላቅሎ 130 ጨዋታዎችን ማድረግ የቻለ ሲሆን 50 ጎሎችንም በውሃ ሰማያዊው መለያ አስቆጥሯል፡፡
በበርካታ ረብጣ ሚልዮኖች ታላላቅ ከዋክብትን ሰብስቦ በነበረው ሲቲ ቤት በአጉዌሮና ካርሎስ ቴቬዝን በመሳሰሉ አጥቂዎች እምብዛም የመጫወት ዕድልን ያላገኘው ቦስኒያዊ ወደጣልያን አምርቶ የተለመደ ጎል አስቆጣሪነቱን የቀጠለ ሲሆን በዚህም ቆይታው የመጀመሪያ እግር ኳሰኛ የሆነበትን አጋጣሚ አሳክቷል፡፡

Advertisements

ዘውዱ በሬሳ View All

ዘውዱ በሬሳ የኢትዮአዲስ ስፖርት ድረ-ገፅ የስፖርት ፀኃፊና ኤዲተር ነው፡፡

%d bloggers like this: