እንቅስቃሴ / ማንችስተር ዩናይትድ የባርሴሎናውን ተከላካይ ለማስፈረም ሙከራ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ

ማንችስተር ዩናይትድ ከክለቡ ጋር ያለው የውል ማራዘሚያ ባለበት የቆመውን የባርሴሎናውን ተከላካይ ሳሙኤል ኡምቲቲን ለማስፈረም ገና ከአሁኑ ጥረት ማድረግ መጀመሩ እየተገለፀ ይገኛል።

ፈረንሳዊው ተጫዋች በካታላኑ ክለብ ያለውን ደሞዝ በእጥፍ ለማሳደግ ቢፈልግም ባርሴሎና የተከላካዩን ፍላጎት የማሳካት እቅድ የሌለው ሲሆን አላማው በ 24 አመቱ ተጫዋች 3.5 ሚሊዮን ፓውንድ አመታዊ ደሞዝ ላይም አነስተኛ ጭማሪ ማድረግ ብቻ ነው። 

ኡምቲቲ እንደ መጀመሪያ ቡድን ተሰላፊነቱ የስፔኑ ክለብ የሚገባውን ክብር እንዳልሰጠው እየተሰማው ከመሆኑ ጋር በተያያዘም ሁኔታው ፈላጊውን ማንችስተር ዩናይትድ ይበልጥ አንቅቶታል። 

ጆሴ ሞውሪንሆ በመጪው ክረምት የመሀል ተከላካይ እና የመሀል አማካኝ በስብስባቸው ላይ ለመጨመር ከመፈለጋቸው ጋር በተያያዘም ኡምቲቲን ወደኦልትራፎርድ ለማምጣት ሙከራ እያደረጉ ይገኛል። 

ኡምቲቲ አሁንም ፍላጎቱ በካታላኑ ክለብ መቆየት ቢሆንም ዩናይትድ የቀድሞውን የሊዮን የኋላ ደጀን ማስፈረም ከፈለገ ከባርሴሎና ጋር መነጋገር ሳይጠበቅበት በውል ማፍረሻው ላይ የተቀመጠውን 60 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 54 ሚሊዮን ፓውንድ መክፈል ብቻ በቂው ነው። 

ዩናይትድ ባሳለፍነው ክረምት በ 30 ሚሊዮን ፓውንድ ቪክተር ሊንድሎፍን ከቤኔፊካ ቢያስፈርምም ስዊድናዊው ተከላካይ የታሰበውን ያህል ማንፀባረቅ አቅቶታል።  

በሌላ በኩል የኦልትራፎርድ ቀዳሚው የመሀል ተከላካይ ምርጫ የሆነው ኤሪክ ቤሊ ከረጅም ጊዜ ጉዳት አገግሞ ቢመለስም ባለበት ተደጋጋሚ ጉዳት እና በተጣማሪዎቹ ግላዊ ችግር የተነሳ ጠንካራ እና ዘላቂ የመሀል ተከላካይ ጥምረት መፍጠር ቸግሮታል።  

Advertisements