የባየርን ሙኒኩ ኮከብ ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ተናገረ

የባየርን ሙኒኩ ኮከብ ተጫዋች ለ”አዲስ ፈተና” ብለቡን ለቆ ሊሄድ እንደሚችል የሚያሳብቅ አስተያየት መስጠቱን ተከትሎ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች የተጫዋቹን ፊርማ ለማግኘት እንደቋመጡ ተሰምቷል፡፡

ኦስትሪያዊው ሁለገብ ተጫዋች ዴቪድ አላባ በባቫሪያኑ ክለብ ወሳኝ ሚና ካላቸው ተጫዋቾች አንዱ ሲሆን ክለቡ ባለፉት አመታት ላገኛቸው ክብሮች አይነተኛ ሚና እንደነበረው አይዘነጋም፡፡

በክለቡ አካዳሚ ተመልምሎ ያደገው የቅጣት ምት ስፔሻሊስቱ አላባ ስለቀጣዩ የእግር ኳስ ህይወቱ ከሚድያ አውታሮች ጋር ባደረገው ቆይታ አዲስ ፈተናና ውድድርን ለመሞከር እንደሚያስብ መናገሩን ተከትሎ ከወዲሁ ከሌሎቹ ግዙፍ ክለቦች ባርሴሎና ፣ ሪያል ማድሪድና ማንችስተር ዩናይትድ ጋር ስሙ እየተያያዘ ይገኛል፡፡

በአገሩ ኦስትሪያ ከሚገኝ ጋዜጣ ጋር በነበረው በዚህ ቆይታ ተጫዋቹ እንደተናገረው በአሳዳጊ ክለቡ እጅግ ደስተኛ መሆኑን ገልጾ ወደሌላ ሊግ ሄዶ አዳዲስ ልምዶችን መቅሰም ግን ፍላጎቱ መሆኑን ያሳየበትን አስተያየት ሰጥቷል፡፡

Advertisements