ፒኤስጂ ከ ሪያል ማድሪድ | የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

ሪያል ማድሪዶች አንድ የግብ ልዩነት ብቻውን በተከታታይ ለስምንተኛ የውድድር ዘመን ወደሩብ ፍፃሜው እንደሚያሳልፋቸው በማወቅ በሻምፒዮንስ ሊጉ 16 ክለቦች ተሳታፊ በሚሆኑበት የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ማክሰኞ ምሽት ወደፈረንሳይ በማምራት ፒኤስጂን ይገጥማሉ።

የአድራን ራቢዮትን ቀዳሚ የፒኤስጂ ግብ የሚያጣፋ ግብ በሮናልዶ ከተቆጠረ በኋላ በጨዋታው መገባደጃ ሰዓት ተከታትለው በተቆጠሩ ሁለትኛው የሮንልዶና የማርሴሎ ተጨማሪ ግቦች ሎስ ብላንኮዎቹ ለተከታታይ ሶስተኛ ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ለማንሳት የሚየደርጉትን ጉዞ ለማስቀጠል ተቃርበዋል።

የዚነዲን ዚዳኑ ቡድን በፈረንጆቹ ጥር ወር አጋማሽ በበርናቢው ስታዲየም ፒኤስጂን ከረታ ወዲህ ከአንድ ሰምንት በፊት በኢስፓኞል 1ለ0 ሲሸነፍ፣ ሌሎች አራት ጨዋታዎችን ደግሞ ማሸነፍ ችሏል።

በአንፃሩ ፒኤስጂ በስፔኑ መዲና ከደረሰበት ሽንፈት በኋል ያካደረጋቸውን አራት ጨዋታዎችን በሙሉ ሲያሸንፍ፣ በእነዚህ ጨዋታዎች ላይ ደግሞ መረቡን ያስደፈረው ሁለት ጊዜ ብቻ ነበር። ይሁን እንጂ በዚህ ሂደት ላይ ወሳኙን የፊት ተጫዋቹን ኔይማርን በረጅም ጊዜ ጉዳት አጥቶታል።

የከዚህ ቀደም አይረሴ ጨዋታቸው

ሪያል ማድሪድ 3-1 ፒኤስጂ (የካቲት 2018)

ይህ ጨዋታ የተደረገው ምንም እንኳ ከሶስት ሳምንታት በፊት የነበረ ቢሆንም፣ ሪያል ማድሪድ ፒኤስጂን 3ለ1 በሆነ ውጤት በበርናቢዩው የረታበት ጨዋታ በልዩ መዝገብ ላይ የሚሰፍር ነው። ምክኒያቱ ደግሞ ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም በነጥብ ጨዋታ ላይ መገናኘት የቻሉት ለሁለት ጊዜያት ብቻ በመሆኑ ነው።

በዚህ ጨዋታ ከኪሊያን ምባፔ የተቀበለውን ግብ አድሪያ ራቢዮት ኬሎር ናቫስ ሊያጨናግፋት ያልተቻለውን ኳስ በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ከመረብ ላይ በማሳረፍ የፈረንሳዩን ክለብ ቀዳሚ ማድረግ የምትችልና ከሜዳ ውጪ የተቆጠረች ጠቃሚ ግብ ማስቆጠር ችሎ ነበር።

ይሁን እንጂ ሪያል ማድሪድ የጨዋታው አጋማሽ ሊጠናቅቅ ሲል ባገኘው የፍፁም ቅጣት ምት በክርስቲያኖ ሮናልዶ አማካኝነት ወደግብ ቀይሮ በአቻ ውጤት ለእረፍት ወጥቷል።

ከእረፍት መልስ የኡናይ ኤምሬው ቡድን የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ወስዶ አሸናፊ ለመሆን ጥረት ቢያደርግም በጨዋታው መገባደጃ ሰዓት ዳግመኛ ባስቆጠረው ክርስቲያኖ ሮናልዶና ማርሴሎ በሶስት ደቂቃዎች ልዩነት በተቆጥሩ ግቦች ተሸናፊ ሆኗል።

ቁልፍ ፍልሚያ

ማቲዮ ኮቫቺች ከ አድሪያን ራቢዮት

ምንም እንኳ ቶኒ ክሩዝና ሉካ ሞድሪች እሁድ ዕለት ወደልምምድ ቢመለሱምና በፓሪሱ ጨዋታ ላይ ተጣምረው እንደሚጫወቱ ቢጠበቅም፣ ዚዳን ወደልምምድ የተመለሱትን ሁለቱን ተጫዋቾች በዚያ ቁልፍ ቦታ ላይ በዚህ ፍጥነትማጫወቱ ከፍተኛ አደጋ እንዳለው በሚገባ ሊየሳስበው ይችላል።

በመሆኑም ፈረንሳያዊው አሰልጣኝ አሴንሲዮን እና ኢስኮን ከካሴሚሮ እና ሚቲዮ ኮቫቺች ጋር አራት አማካኞችን በማጫወት ስልቱ አማራጭ ሊያደርግ ይችላል። በመሆኑም ካሴሜሮና ኮቫቺች በአማካኝ ተከላካይነት ሚናው የፒአስጂ አቻዎቻቸውን የመግታት ሚና እንደሚኖራቸው ይጠበቃል።

ኮቫቺችም በዚህ የውድድር ዘመን በተደረጉ ያለፉት አራት ጨዋታዎች ላይ ሙለ 90 ደቂቃዎችን መጫወት ችሏል።

ትውለድ ኦስትሪያዊ የሆነው የክሮሺፓ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቹ ኮቫቺች ሪያል ማድሪድ በቀድመው ጨዋታ በፓሪሱ ክለብ እጅ እንዳይሰጥ በማድረጉ ሚና ላይም የነበረው ተሳትፎ ከፍ ያለ ነበር። የፈረንሳያዊው ድንቅ ወጣት አማካኝ፣ ራቢዮትን እንቅስቃሴ ለመግታትም ከሞድሪች ወቅታዊ የአካል ብቃት አንፃር ሁነኛ ተጫዋች እንደሚሆንም ይጠበቃል።

የቡድን ዜናዎች

ምንም እንኳ ክሩዝና ሞድሪች በማክሰኞ ምሽቱ ጨዋታ ላይ መሰለፋቸው አጠራጣሪ ቢሆንም ወደልምምድ መመለሳቸውን ተከትሎ ተከላካዩ ኼሱስ ቫሌኾ ከዚዳኑ የቡድን ስብስብ ውጪ የሆነ ብቸኛው ተጫዋች ያደርገዋል። የ21 ዓመቱ ተጫዋች አሁንም ባለበት ጉዳት በዚህ ጨዋታ ላይም የማይሰለፍ ይሆናል።

የመጀመሪያው ጨዋታ በቅጣት ምክኒያት ያለፈው ዳኒ ጃርቫኻልም በዚህ ጨዋታ ወደሜዳ የሚመለስ ተጫዋች ነው።

ባለሜዳዎቹ የቀዶ ህክምና ማድረጉና ከሶስት ወራት ወዲህ ወደሜዳ እንደማይመለስ በይፋ ያሳወቁትን ኔይማርን በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፉ ሲሆን፣ በእሱ ፈንታ ኤንጅል ዲ ማሪያን ይጥቀማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል ከኡናይ ኤምሬው ቡድን ብቸኛው መሰለፉ የሚያጠራጥር ተጫዋች ኻቪየር ፓስቶሬ ነው። ይህ ማለት ደግሞ ክለቡ በሰምንቱ መጨረሻ ትሮይስን 2ለ0 በረታበት ጨዋታ ላይ ያልተሰለፈው ኪሊያን ምባፔ በዚህ ጨዋታ ላይ የመጀመሪያ ተስላፊ ሆኖ ሊጫወት ይችላል። እንዲሁም በመጀመሪያው ጨዋታ ላይ በጉዳት ምክኒያት ያልተሰለፉት ልምድ ያላቸው ሁለቱ አንጋፋ ተጫዋቾች ላሳና ዲያራና ቲያጎ ሞታ ለዚህ ጨዋታ ዝግጁ ናቸው።

የጨዋታ ግምት

ፒኤስጂዎች ከሶስት ሳምንት በፊት በስፔኑ ጨዋታ ከፍተኛ የኳስ ብልጫ ነበራቸው። ይህ የኳስ ቁጥጥር የበላይነትም ዳግመኛ እንደሚኖር ይጥበቃል።

ሪያል ማድሪዶች በይበልጥ የመልሶ ማጥቃት አጭዋወት ዘዴን የሚመርጡ ሲሆን፣ ነገር ግን ለ ፓሪሲየኖቹ ግብ የማያስቆጥሩ ከሆነ መረብን የመፈተሹ ስራ የሎስ ብላንኮዎቹ ይሆናል። እንግዳዎቹ በድኖችም ድንገተኛ የግብ ዕድል ሲፈጥሩ ብንመለከት የሚያስገርም ነገር አይሆንም። በተለይም የአጥቂ ክፍላቸው በመጨረሻው የግብ ክልል ላይ ዕድሎችን ደጋግሞ መፍጠር የሚችል ከሆነ።

ከሁለቱ አንዱ ክለብ በጊዜ ግብ የሚያስቆጥር ከሆነም በጨዋታው ድባብ ላይ ፍፁም ለውጥ ሊፈጥር ይችላል። ነገር ግን ሎስ ብላንኮዎቹ በእንዲዚህ ዓይነቱ ጨዋታ ላይ የካበተ ልምድ ያላቸው በመሆኑ በጨዋታው ላይ ጎልተው መውጣታቸው አይጠረጠርም።

ግምታዊ ውጤት፡ ፒኤስጂ 0-2 ሪያል ማድሪድ

Advertisements