“ህልም አለኝ ” – ማውሪሲዮ ፖቾቲንሆ

Image result for pochettino

ፅሁፍ ዝግጅት :  በመንሀጁል ሀያቲ

የቶትንሀም ሆትስፐርሱ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቾትኖ ተጨዋቾቹ ህልም እንዲኖራቸው እና የቻምፒዬንስ ሊጉን ዋንጫ ማንሳት እንችላለን ብለው እንዲያስቡ እንደሚፈልግ ተናገረ ፡፡

አርጀንቲናዊው የቀድሞ የኤስፓኞል አለቃ ሞሪሲዬ ፖቸቲኖ አጥቂው ሀሪ ኬንን እና የቡድን አጋሮቹን ትልቅ ህልም እንዲያልሙ እና የቻምፒዬንስ ሊጉን ዋንጫ ማንሳት እንችላለን ብለው ማሰብ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

” እኔ ህልመኛ ነኝ፤ በቻምፒዬንስ ሊጉ ጥሩ ነገርን መስራት ችለው ካጠናቀቁ ተጨዋቾቹ ጀግኖች ይሆናሉ።   በእያንዳንዷ ያገኛሀት እድል እሩቅ ለመሄድ መሞከር አለብህ ፤ እኛ ጥሩ ቡድን ነን የቻምፒዬንስ ሊጉን ዋንጫ እናነሳዋለን ብለን ማሰብ አለብን፤ ሁሌም የምናስበውም ይህንኑ ነው።”  ያሉ ሲሆን

“ባለፉት ሲዝኖች ጥሩ ተፎካካሪ መሆን እንደምንችል አሳይተናል፤ አሁንም ጠንካራ መሆን ይጠበቅብናል፤ የምንገጥመው ከአለማችን ምርጥ ከሆኑት ቡድኖች አንዱን ነው. ነፃ ሆነን ማሰብ ይገባናል፤ ይህንን ማድረግ ከቻልን እና ጥሩ ጨዋታ ከተጫወትን የማሸነፉ እድል አለን።” ሲሉ ሀሳባቸውን አገባደዋል፡፡

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ዛሬ ምሽት 4፡45 በዌምብሌይ ስቴዲየም የጣሊያኑን ክለብ ጁቬንቱስን የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡

Advertisements