ቶተንሃም ከ ጁቬንቱስ| የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

የማውሪሲዮው ፖቸቲኖው ቶተንሃም ረቡዕ ምሽት በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር የሻምፒዮንስ ሊግ 16 ክለቦች ተሰታፊ የሚሆኑበት የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ከጁቬንቱስ ጋር በቱሪን 2ለ2 የተለያየበትን መልካም አጋጣሚ በእጁ ይዞ በዌምቤሌይ የሚፋለም ይሆናል።

የቡድን ዜናዎች

ቶተንሃሞች ባለበት የቋንጃ ጉዳት ምክኒያት ይህን ጨዋታ ያለተከላካያቸው ቶቢ አልደርዊረልድ የሚያደረጉ ይሆናል።

ያን ቨርቶንግኸን ከጉዳት ተመልሶ ቅዳሜ ኸደርስፊልድን 2ለ0 ማሸነፍ በቻሉበት ጨዋታ ላይ ሙሉ ዘጠና ደቂቃ መጫወቱን ተከትሎ ዛሬ ምሽት ከጁቬንቱስ ጋር በሚደረገው ጨዋታ ላይም የመጀመሪያ ተሰላፊ እንደሚሆን ይጠበቃል።

አርጄንቲናዊው የስፐርስ አሰልጣኝ በግራ ክንፍ የአጥቁነት ሚና ላሜላን አሊያም ሶንን የመጀመሪያ ተሰላፊ ለማድረግ ውሳኔ የማሳለፍ ከባድ ፈተና ያለባቸው ቢሆንም፣ የ46 ዓመቱ አሰልጣኝ ግን ለባለፈው ቅዳሜ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ክለቡ አሸናፊው እንዲሆን አብይ ምክኒያት የነበረውን ኮሪያዊውን ተጫዋች ምርጫቸው እንደሚያደርጉ ይጥበቃል።

በሌላ በኩል የማሲሚላኖ አሌግሪው ጁቬንቱስ ወደሩብ ፍፃሜው የማለፍ ተስፋ እንዲኖረው በሚገባ መረቡን ባለማስደፈር ከሜዳው ውጪ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ግቦችን ማስቆጠር ይጠበቅበታል።

ዕድሜ ጠገቧ እመቤት ለረቡዕ ምሽቱ ጨዋታ ያለባት አዲስ አሳሳቢ ጉዳት የለም። ይሁን እንጂ በርናዴሺ፣ ኩዋድራዶ እና ደ ሲጊሊዮ ግን አሁንም ባለባቸው የከረመ ጉዳት ከሜዳ እንደራቁ ይቆያሉ።

ይሁን እንጂ ሄጉዌን በገጠመው የቁርጭምጭሚት ጉዳት ምክኒያት ጁቬንቱስ በሳምንቱ መጨረሻ ላዚዮን 1ለ0 ማሸነፈ በቻለበት የሴሪ ኣ ጨዋታ ላይ ባይሰለፍም በዚህ ወሳኝ የሻምፒዮንስ ሊግ የምሽት ጨዋታ ላይ እንደሚመለስ ግን ይጠበቃል።

ግምታዊ አሰላለፎች

የቶተንሃም የመጀመሪያ ግምታዊ አሰላለፍ (4-2-3-1):

ግምታዊ የመጀመሪያ ተሰላፊዎች

ሎሪስ (ግብ ጠባቂ)

ኦሪየር (ቀኝ ተከላካይ)፣ ሳንቼዝ (ቀኝ የመኃል ተከላካይ)፣ ቨርቶንግኸን (ግራ የመኃል ተከላካይ)፣ ዴቪስ (ግራ ተከላካይ)

ዴምቤሌ (የመኃል የተከላካይ አማካኝ)፣ ዳየር (የመኃል ተከላካይ አማካኝ)

ኤሪክሰን (የግራ ክንፍ የፊት ተጫዋች)፣ አሊ (የመኃል አጥቂ አማካኝ)፣ ሶን (የግራ ክንፍ የፊት ተጫዋች)

ኬን (አጥቂ)

የጁቬንቱስ ግምታዊ የመጀመሪያ አሰላለፍ
(4-3-2-1)

ግምታዊ የመጀመሪያ ተሰላፊዎች

ቡፎን (ግብ ጠባቂ)

አሳሞሃ (ግራ ተከላካይ)፣ ቼሊኒ (ግራ የመኃል ተከላካይ)፣ ቤናሺያ (ቀኝ የመኃል ተከላካይ)፣ ሊችስቴነር (ቀኝ ተከላካይ)

ማቲዩዲ (ግራ የመኃል ተከላካይ)፣ ፒያኒች (የመኃል አማካኝ ተከላካይ)፣ ክኸዲራ (ቀኝ የመኃል አማካኝ)

ዲባላ (ግራ አማካኝ)፣ ማንዙኪች (ቀኝ አማካኝ)

ሄጉዌን (አጥቂ)

ጨዋታው በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት 4፡45 ይጀምራል።

Advertisements