የሊቨርፑሉ ኮከብ ሙሀመድ ሳላህ ለግብፅ የህፃናት ሆስፒታል £ 500,000 ፖውንድ በእርዳታ ሰጠ።

​በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብ በመጫወት ላይ የሚገኘው አፍሪካዊዬ የግብፅ ኮከብ ሙሀመድ ሳላህ በግብፅ ውስጥ ለሚገኝ የህፃናት ሆስፒታል £500,000 ፖውንድ ወደ ግብፅ ገንዘብ ሲቀየር 12 ሚሊዬን የግብፅ ፖውንድ በእርዳታ ስጥቷል።
ለሆስፒታሉ በድጋፍ የተስጠው 12 ሚሊዬን የግብፅ ፖውንድ በግብፅ ካይሮ ውስጥ ለሚገኘው ሆስፒታል አዳዲስ የተለያዩ የህክምና እቃዋችን ለመግዛት እንደሚውል ከእርዳታው ጋር በተያያዘ በሶሻል ሚዲያ ይፋ ያደረጉት የሆስፒታሉ ሀላፊ ሙስጠፋ ዘምዘም አስታውቀዋል።

ሙሀመድ ሳላህ በሀገሩ ግብፅ የተለያዬ ጥሩ ስራዋችን በመስራት በግብፅ በጀግናነት ስሙን እየገነባ ይገኛል ፤ ሳላህ አሁን እየተጫወተ ባለበት የሊቨርፑል ቤትም አስደናቂ አቋምን እያሳየ ይገኛል፤ በተሰለፈባቸው 38 ጨዋታዋች 32 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

ሙሀመድ ሳላህ ሀገሩ ግብፅ በቅርቡ ለሚካሄደው ሩሲያ ለምታዘጋጀው የ2018ቱ የአለም ዋንጫ እንድታልፍ ትልቁን ሚና መጫወቱ የማይዘነጋ ነው።

Advertisements