“ሊቨርፑሎች በሻምፒዬንስ ሊጉ ማንችስተር ሲቲን ሳይሆን ሌሎች ሶስት ቡድኖችን ነው መፍራት ያለባቸው “- ማይክል ኦውን

Image result for owen

የቀድሞው የማንችስተር ዬናይትድ እና የሊቨርፑል ተጨዋች የነበረው ማይክል ኦይን በሻምፒዬንስ ሊጉ የሩብ ፍፃሜ ፍልሚያ ላይ ሊቨርፑሎች ሊፈሯቸው ይገባል ያላቸውን ሶስት ቡድኖች ይፋ አድርጓል።

እንደ ቀድሞ የሊቨፑል ኮከብ ማይክል ኦውን እምነት ከሆነ ሊቨርፑሎች ሊፈሩ የሚገባው አሁን በፕሪሚየር ሊጉ ምርጥ ግስጋሴ እያደረጉት ያሉትን ማንችስተር ሲቲዋችን ሳይሆን ሌሎች ሶስት ክለቦችን ነው ሲል ለቢቲ ስፖርት ሀሳቡን ሰጥቷል፡፡

” ማን ወደ ሩብ ፍፃሜው እንደሚገባ ለማወቅ ቢያስቸግርም ፤ ሊቨርፑሎች ሪያል ማድሪድን፤ ባርሴሎናን እንዲሁም ባየር ሙኒክን ሊፈሯቸው ይገባል፤ ማንችስተር ሲቲን ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው ፤ ሲቲ ስጋት አይሆንባቸውም።”  ሲል ከሲቲ ይልቅ ሶስቱ ቡድኖች ፈታኝ እንደሆኑ አብራርቷል፡፡

በአንፃሩ ሊቨርሎች  ወደ ሩብ ፍፃሜ መግባታቸውን ተከትሎ የርገን ክሎፕ በሰጡት አስተያየት የትኛውም ቡድን በሩብ ፍፃሜው ቢደርሳቸው ምንም እንደማያስጨንቃቸው  ማሳወቃቸው ይታወሳል፡፡

Advertisements