የሊቨርፑሉ ኮከብ ሳይዶ ማኔ ለቀያይ ሰይጣኖቹ ማስጠንቀቂያ ልኳል።

FBL-EUR-C1-LIVERPOOL-SPARTAK

ፅሁፍ ዝግጅት :  በመንሀጁል ሀያቲ

የሊቨርፑሉ ኮከብ ሳይዶ ማኔ ማንችስተር ዬናይትድ ሊቨርፑልን በኦልድ ትራፎርድ በሚያስተናግድበት የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ ለቀያይ ሰይጣኖቹ ማስጠንቀቂያ ልኳል።

ሰይዶ ማኔ ሊቨርፑል አሁን ባለው አቋም የትኛውንም ቡድን ማሸነፍ ይችላል፤ ለየትኛውም ክለብ እጅ አይሰጥም በማለት ማንችስተር ዬናይትዶችን አሰጠነቀቀ።

ቀዬቹ የየርገን ክሎፕ ልጆች በአስተማማኝ ሁኔታ ፖርቶን በአጠቃላይ የ 5 ለ 0 ውጤት በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍፃሜ ማለፍ የቻሉ ሲሆን፤ በፕሪሚየር ሊጉ ቀጣይ ጨዋታቸውን ከማችስተር ዬናይትድ ጋር የሚያደርጉ ይሆናል።  ይህንንም ጨዋታ ተከትሎ የሊቨርፑሉ ኮከብ ሰኢዶ ማኔ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥቷል ።

” ቀላል ላይሆን ይችል ይሆናል ነገር ግን ሁሌም እንደምለው አሁን ባለን አቋም አለም ላይ ያለ የትኛውንም ቡድን ማሸነፍ እንችላለን።”

” የእውነት ለመናገር ማንችስተር ዬናይትድ በእንግሊዝ ውስጥ ካሉ ክለቦች ምርጡ ክለብ ነው በእንግሊዝ ብቻም ሳይሆን በአለም ላይ ካሉም ምርጥ ነው ።”

” እንደዚህ አይነት ጨዋታ መጫወት ለማንኛውም ተጨዋች ህልም ነው፤ ስለዚህ ሁላችንም ስለጨዋታው ወደ ፊት እንመለከታለን።” በማለት ሀሳቡብ ቋጭቷል፡፡

ሰይዶ ማኔ እንደሚታወሰው በያዝነው የውድድር ማንችስተር ዬናይትድ ወደ አንፊልድ ተጉዞ ሊቨርፑልን በገጠመበት እና ሁለቱ ቡድኖች አቻ በወጡበት ጨዋታ ላይ በጉዳት ምክንያት መሰለፍ አልቻለም ነበር።

Advertisements