የቶተንሃሙ ኋይት ሃርት ሌን ስታዲየም የማስፋፊያ ግንባታ ሂደት በፎቶግራፍ

በዳንኤል ሌቪ ኃላፊነት የሚመራው የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም ሆትስፐርስ የቀድሞ ኃይት ሃርት ሌን የተሰኘውን ስታዲየሙን ሙሉ በሙሉ በማፍረስ በዚያው ስፍራ ላይ አዲስ የስታዲየም ግንባታ ፕሮጀክት በማከናወን ላይ ይገኛል።

ክለቡ በማስፋፊያ ግንባታው ቀደሞ 36,284 መቀመጫዎች የነበረውን ስታዲየም 61,559 መቀመጫዎች እንዲኖሩት አደርጎ በመሰራት ላይም ይገኛል።

የስታዲየም ግንባታው ተጠናቆ ወደአገልግሎት ሲገባ ለክለቡ ከሚሰጠው የእግርኳስ ጫዋታ አገልግሎት በተጨማሪ ለሌሎች ስፖርቶች እና የተለያዩ የሙዚቃ ኮንሰርቶች አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ ከመዘጋጀቱ በተጨማሪ የመጫወቻ ሜዳው በ25 ሰከንዶች ውስጥ ወደሶስት ቦታ የሚከፋፈል ወለል እንዲኖረው ተደርጎ የሚዘጋጅም ነው።

በአሁኑ ጊዜ ክለቡ በይፋዊ ድረገፁ የለቀቀውን የዚህን በልዩ ጥበብ ነባሩን እንደአዲስ አፍርሶ በማስፋፋት የመገንባት የኪነ ህንፃ የጥበብ ስራ ሂደት ከታች ባሉት ምስሎች ይቃኙ ዘንድ ጋበዝን።

የኋይት ኃርት ሌን የማስፋፋያ ግንባታ ሂደት


Advertisements