ማንችስተር ዩናይትድ ከ ሊቨርፑል | የፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

ይህ ጨዋታ በሁለቱ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቀንደኛ ተቀናቃኝ ክለቦች ማንችስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል መካከል የውድድር ዘመኑን በሁለተኝነት ለማጥናቀቅ ታላቅ ፍልሚያ የሚያደረግበት በኦልድትራፎርድ የሚካሄድ ጨዋታ ነው።

ይህ ጨዋታ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙት ማንችስተር ዩናይትዶች በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ከመመራት ተነስተው ክሪስታል ፓላስን 3ለ2 በሆነ ውጤት ካሸነፉ በኋላ የሚያደርጉት ይሆናል።

ሊቨርፑሎች በፕሪሚየር ሊጉ ያደረጓቸውን ተከታታይ ሶስት ጨዋታዎች ማሸነፍ ቢችሉም ማክሰኞ ምሽት በሻምፒዮንስ ሊጉ ከፓርቶ ጋር 0ለ0 በማጠናቀቅ የድል ጉዟቸው ተገቷል።

የቅዳሜው ጨዋታ በሊግ ውድድር ላይ በሁለቱ ክለቦች መካከል የሚደረግ 170ኛ የጨዋታም ነው።

ጨዋታው ምን ይመስላል?

ይህ የቅዳሜ ዕለት ጨዋታ በሁለቱ ክለቦች መካከል ካለው የመረረ ተቀናቃኝነት ባሻገር ለሁለቱም ክለቦች ጉልህ ፋይዳ ያለው ጨዋታ ነው። ምክኒያቱም ጨዋታው በውድድር ዘመኑ ከሁለቱ ክለቦች ቀዳሚ ሆኖ የሚያጠናቅቅውን ቡድን የሚጠቁም በመሆኑ ነው።

በዚህ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ከወዲሁ የሊጉን ክብር መቀዳጀቱ እውን የሚመስለው ማንችስተር ሲቲ ከሁለቱ ክለቦች በብዙ የነጥብ ልዩነት በመራቅ ደረጃ ሰንጠረዡ ላይ በቀዳሚነት ተቀምጧል።

ዩናይትዶች ከቀዮቹ ጋር በሜዳቸው ባደረጓቸው 13 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በአስሩ አሸናፊ ሲሆኑ በ2008-09 እና 2013-14 የውድድር ዘመኖች ደግሞ ሽንፈት ደርሶባቸውል። እንዲሁም ባለፈው የውድድር ዘመን ያደረጉትን ጨዋታ ደግሞ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል።

ማንችስተር ሲቲዎች ብቻ ከየርገን ክሎፑ ቡድን ከፍ ያለ ግብ ያስቆጠሩ ቢሆንም፣ ከሜዳቸው ውጪ ባስቆጠሯገው ግቦች ግን ቀዮቹ ከየትኞቹም የሊጉ ክለቦች የላቁ ናቸው።

እንዲሁም ሊቨርፑሎች ከወዲሁ በሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ መሳተፍ የሚያስችላቸውን ትኬትም መቁረጥ ችለዋል። በሌላ በኩል ዩናይትዶች ከመርሲሳይዱ ተጋጣሚያቸው ጋር ከተጫወቱ የሶስት ቀናት ልዩነት በኋላ የሻምፒዮንስ ሊግ የመልስ ጨዋታቸውን በኦልድትራፎርድ የሚጫወቱ ይሆናል።

ጨዋትውን እንዴት በቀጥታ መከታተል ይችላሉ?

በአፍሪካ ከሰሀራ በታች (ኢትዮጵያን ጨምሮ ) ነዋሪ ከሆኑ ይህን ጨዋታ በመልቲቾይዙ ሱፐር ስፖርት 3፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ ሆነው የሚመለከቱ ከሆነ ቢኢንስፖርት 11፣ በዩናይትድ ኪንግደም ኗሪ ከሆኑ ደግሞ በስካይ ስፖርት ሜንኤቨንት የቲቪ ቻናል እና በስካይ ጎ የኢንተርኔት ስትሪሚንግ እንዲሁም ነዋሪነቶ በሰሜን አሜሪካ ከሆነ በኤንቢሲ ስፖርትስና እና በፉቦ ቲቪ በቀጥታ ጨዋታውን መመልከት ይችላሉ።

ቡድኖቹን የተመለከቱ ዜናዎች

የማንችስተር ዩናይትድ የቡድን ስብስብ

ግብ ጠባቂዎች፡ ደህያ፣ ሮሜሮ፣ ፔሬራ
ተከላካዮች፡ ሊንደሎፍ፣ ቤሊ፣ ጆንስ፣ ስሞሊንግ፣ ሮኾ፣ ሻው፣ ቫሌንሺያ፣ ዳርሚያን
አማካኞች፡ ፓግባ፣ ማታ፣ ሊንጋርድ፣ ካሪክ፣ ያንግ፣ ማቲች፣ ማክቶሚናይ፣ ጎሜስ፣
የፊት ተጫዋቾች፡ ራሽፎርድ፣ ማርሺያል፣ ሉካኩ፣ ኢብራሂሞቪች፣ ሳንቼዝ

ሞሪንሆ ከቼልሲ ጋር ሲጫወቱ እንዳደረጉት ሁሉት የአማካኝ ክፍላቸውን የዳይመንድ ቅርፅ በማስያዝ በማጥቃቱ እንቅስቃሴ ላይ ብልጫ የሚወስዱበትን ቀመር የማግኘት የቤት ስራ ያለባቸው ሲሆን፣ የ4-3-3 አሰላለፍም ሊጠቀሙ እንደሚችሉም ይጠበቃል።

ዩናይትድ ይህን ጨዋታ በጉዳት ላይ የሚገኙትን አንደር ሄሬራ፣ ማሩዋን ፌላኒን እና ዳሌይ ብሊንድን ሳይዝ የሚጫወት ሲሆን፣ ፓላስን ድል ባደረጉበት የሰኞ ምሽት ጨዋታ ላይ ያልተሰለፈው አንቶኒ ማርሻል በዚህ ጨዋታ ላይ የመጀመሪያ ተሰላፊ የመሆን ዕድሉ አነስተኛ ነው።

ግምታዊ የመጀመሪያ ተሰላፊዎች፡ ደ ኽያ፣ ቫሌንሺያ፣ ቤሊ፣ ስሞሊንግ፣ ያንግ፣ ማክ ቲሞኒ፣ ማቲች፣ ፖግባ፣ ሊንጋርድ፣ ሉካኩ፣ አሌክሲስ

የሊቨርፑል የቡድን ስብስብ

ግብ ጠባቂዎች፡ ካሪዩስ፣ ሚኞሌ፣ ዋርድ
ተከላካዮች፡ ክላይን፣ ቫንዳይክ፣ ሎቭረን፣ ጎሜዝ፣ ክላቫን፣ ሞሬኖ፣ ሮበርትሰን፣ ማቲፕ፣ አሌክሳንደር-አንርኖልድ
አማካኞች፡ ዋይናልደም፣ ሄንደርሰን፣ ሚልነር፣ ላላና፣ ኦክስሌድ-ቻምበርሌን፣ ቻን፣ ዉድባርን፣ ፓውሊንሆ
የፊት ተጫዋቾች፡ ሳላህ፣ ማኔ፣ ኢንግስ፣ ሶላንኬ፣ ብሬውስተር

ሊቨርፑል በዚህ የውድድር ዘመን በሚገባ እያገለገሉት የሚገኙትን ሶስቱን የፊት ተጫዋቾቹን በፊት ለፊት በኩል ያሰልፋል። መሐመድ ሳላህ እና ሳዲዮ ማኔ በፊርሚኖ ግራና ቀኝ በኩል ሆነው የሚጫወቱም ይሆናል።

በዚህ ጨዋታ ላይ ጆርጂኒዮ ዊናልደም ይሰለፋል ተብሎ ባይጠበቅም፣ ከፖርቶ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ላይ እንዲያርፍ የተደረገው ኦክስሌድ-ቻምበርሌን ወደመጀመሪያ ተሰላፊነት ሚና እንደሚመለስ ይጠበቃል።

ግምታዊ የመጀመሪያ ተሰላፊዎች፡ ካሪዩስ፣ አሌክሳንደር-አርኖልድ፣ ማቲፕ፣ ቫን ዳይክ፣ ሮበርትሰን፣ ኦክስሌድ-ቻምበርሌን፣ ሄንደርሰን፣ ቻን፣ ሳላህ፣ ፊርሚኖ፣ ማኔ

Advertisements