” ሜዳ ላይ የሞሪንሆ ወታደር ነኝ” – ሮሜሎ ሉካኩ

Image result for lukaku

የማንችስተር ዬናይትዱ አጥቂ ሮሜሎ ሉካኩ ” ሜዳ ላይ የሞሪንሆ ወታደር ነኝ ፤ እኔም ከራሴ በፊት ለቡድኑ ቅድሚያን እሰጣለሁ።” በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል

ጽኁፍ ዝግጅት :-  መንሀጁል ሀያቲ

እኔም ከራሴ በፊት ለቡድኑ ቅድሚያን እሰጣለሁ።” በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል ቤልጄማዊዬ ግዙፉ አጥቂ ሮሜሉ ሉካኩ በያዝነው የውድድር ዘመን ለማንችስተር ዬናይትድ አጠቃላይ 23 ጎሎችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን ማንችስተር ዬናይትድ ከሊቨርፑል ጋር ለሚያደርገው ፍልሚያ በሙሉ አቅሙ ቡድኑን ለመርዳት ዝግጁ መሆኑን ገልፃል።

ሉካኩ ከስካይ ስፖርት ጋር ባደረገው ሰፋ ያለ ቆይታም   ” አሰልጣኜ ሜዳ ላይ እኔ የእሱ ወታደር እንደሆንኩ ያምናል፤ እኔም ሁሌ ከእራሴ በላይ ቡድኑን አስቀድማለሁ ይህንንም ለአሰልጣኜ ሁሌም ነግረዋለው።” ” ለቡድኑ ጥሩ እየሰራው እገኛለው፤ ሞሪንሆም ለእኔ በጣም ጥሩ ነው እሱም ይህ የወታደርነት አስተሳሰብ እንዳለኝ ያውቃል ነገር ግን እኔ አጥቂ ነኝ አሁንም ጎሎችን ማስቆጠር አለብኝ።”

ሮሜሎ ሉካኩ ማንችስተር ዬናይትድ ባደረጋቸው ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጨዋታዋች ላይ ለማንችስተር ሁለት ጎሎችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን፤ ማንችስተር ዬናይትድ በኦልድ ትራፎርድ ከቸልሲ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይም ጎል በማስቆጠር ከትላልቆቹ ቡድኖች ላይ ጎላ ያለማግባት ትችትን ውድቅ ማድረግ ችሏል፡፡

Advertisements