ሮማን አብራሞቪች አንቶኒዬ ኮንቴ በአንድ ሁኔታ ላይ ከተስማሙ በቸልሲ የአሰልጣኝነት ስራቸው ሊያቆዬቸው ይፈልጋሉ

Image result for antonio conte

የ2016/2017 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሻምፒዬኖቹ ቼልሲዋች አሰልጣኝ አንቶኒዬ ኮንቴ አሁን በቸልሲ ቤት ከምንግዜውም በላይ በከፍተኛ ጫና ውስጥ ነው የሚገኙት፤ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ካደረጓቸው ሁለት ጨዋታዋች ውስጥ በሁለቱ የማንችስተር ከተማ ክለቦች ሽንፈትን ቀምሰዋል።

ቸልሲ በሊጉ 4ተኛ ላይ ከሚገኘው ቶትንሀም በ5 ነጥብ ተበልጦ በ53 ነጥብ 5ተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን እስከ 4ተኛ ደረጃ በመያዝ ለቀጣይ አመት ሻምፒዬንስ ሊግ የመግባት እድላቸው አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል።   ይሁን እንጅ እንደ ዘሰን ዘገባ ከሆነ ከ4ተኛ ደረጃ በታች ሁነው እንኳን ቢጨርሱ አንቶኒዬ ኮንቴ በስታምፎርድ ብሪጅ ለመቆየት የሚያስችል እድል አላቸው ይለናል።

እንደሚታወሰው ጣሊያናዊዬ በይፋ በዝውውር ገበያው ላይ በስፋት መንቀሳቀስ አልቻልኩም በማለት በክለቡ ሀላፊዋች ላይ ትችት መሰንዘራቸው የሚታወስ ነው፤ ይህ ንግግራቸውም ሩሲያዊዩን ባለሀብት ሮማን አብራሞቪችን እና የክለቡን ባለስልጣናት አላስደሰተም።

የቸልሲ ምንጮች ለጋዜጣው በሰጡት መረጃ ፡ ” አሁን አሁን ሮማን አብራሞቪች አሰልጣኞችን በማባረር ደስተኛ አይደሉም፤ ሻምፒዬንስ ሊግ ጥሩ ነገር ነው ግን ውል ማፍረሻ አይሆንም በዚህ ስአት አብራሞቪች ለአሰልጣኙ እያንዳንዱን እድል ይሰጣሉ።”  ” ነገር ግን ችግሩ ያለው ኮንቴ በድጋሚ ቅሬታ የሚያቀርቡ ከሆነ ነው ።” የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ቅዳሜ 2:30 ላይ ከክሪስታል ፖላስ ጋር በሜዳቸው ጨዋታ የሚያደርጉ ይሆናል።

Advertisements