ዣካ አርሰናል ኤሲሚላንን ያሸነፈበትን ሚስጥር ገለፀ

የመድፈኞቹ አማካኝ ግራኒት ዣካ 16 ክለቦች በቀሩት የዩሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ የደርሶ መልስ የመጀመሪያ ጨዋታ ሐሙስ ምሽት ክለቡ ኤስሚላንን ከሜዳው ውጪ 2ለ0 የረታበትን ሚስጥር ገልፅዋል።

አርሰናል ሃሙስ ምሽት በሳንሴሮ 2ለ0 በሆነ ውጤት ድል ከማድረጉ በፊት ያደረጋቸውን ተካታታይ አራት ጨዋታዎች ተሸንፏል።

ይህ በኤሲሚላን ላይ የተቀዳጅው ድል በአሰልጣኙ አርሰን ቬንገር ላይ እየደረሰ ያለውን ጫና በተወሰነ መልኩም ቢሆን የሚያረግብ ነው።

ነገር ግን ከዚህም በላይ ድሉ ለአማካኙ ለግራኒት ዣካ የአርሰናልን እውነተኛ ብቃት የሚያሳይ ነው።

ዣካ ለአርሰናል ይፋዊ ድረገፅ ሲናገር “ብዙ ሰዎች ከውጪ ሆነው ሰእኛ ተናግረዋል። ነገር ግን ቡድኑ ውስጥ ስላለው ነገር ማንም አየውቅም።

“ዛሬ አንድነትን አሳይተናል። በተለያዩ መንገዶች [የአሸናፊነት] መንፋስንም አሳይተናል።

“ሁሉም ሰው የሚያውቀው እነዚያን የደረሱብንን ሽንፈቶች ነው። ያ ደግሞ ለእኛ አስቸጋሪ ነበር። በጋራ መሆናችን እና በውጪ ላሉት ሰዎች አንድ ቡድን መሆናችንን ማሳየታችን ፋይዳ ያለው ነገር ነው።” ብሏል።

በሃሙስ ምሽቱ ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ የተቆጠሩትን ሁለት የአርሰናል ግቦች ሂነሪክ ሚክሂታሪያን እና አሮን ራምሴ ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችለዋል።

Advertisements